Selam Warga / Friday, March 13, 2026 / Categories: CASSATION, Cassation ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 244308 ጉዳዩ በከተማ ክልል የሚገኝ መሬት ይዞታ መብት ለማስከበር የቀረበ ክስ የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ በ14/11/2013 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ስሙ ፊጋ በሚባል ሰፈር አዋሳኞቹ በክስ የተገለፀውን ግምቱ 2000 ካ.ሜ የሆነ የእርሻ መሬት ከደርግ መንግስት ጀምሮ ተገቢውን የመሬት ግብር በመክፈል ስጠቀምበት የቆየሁትን የእርሻ መሬት ለ11 ዓመት ውጭ ሀገር ቆይቼ ግንቦት 2012 ዓ.ም ወደ ሀገር ቤት ስመለስ ይዞታዬን እንዲያስተዳድሩልኝ ተወካይ አስቀምጬ እያለ አመልካች ምንም ህጋዊ መብት እና የውል ግንኙነት ሳይኖረው ግምቱ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ) የሆነውን ያጠርኩትን አጥር ሰኔ ወር 2011 ዓ.ም በማፍረስ ተወካዬንም ከይዞታው በማባረር ግንብ አጥር በማጠር ቤት ሰርቶ በሕገወጥ መንገድ ይዞታዬን የያዘብኝ በመሆኑ ያለፈቃዴ የገነባውን ቤትና አጥር አፍርሶ በፍ/ሕ/ቁ 1206 መሰረት ይዞታዬን ለቆ ያስረክበኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ Previous Article ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የተሰጠ የህግ ትርጉም Next Article ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 271726 Print 4492 Documents to download ሰበር መዝገብ 244308 (1)(.pdf, 551.03 KB) - 967 download(s)
በጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳዮችን እንዲመለከቱ... በጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳዮችን እንዲመለከቱ... Friday, April 16, 2021 3734 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የሚታዩባቸው ችሎቶች በጠቅላይ ፍ/ቤት መደራጀታቸውን አፈጻጸማቸውን በተመለከተ ለፕሬዝደንት ጽ/ቤትና ለሬዲስትራሮች የስራ አቅጣጫ ሰጡ፡፡ Read more
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ2012 በጀት ዓመት... የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ2012 በጀት ዓመት... Tuesday, October 27, 2020 3676 ፍርድ ቤቱ ከእያንዳንዱ ምድብ ችሎቶት በባህሪና በመዝገብ አፈጻጸም መልካም ውጤት ያስመዘገበ 1 ዳኛ በመምረጥ በአጠቃላይ ለ11 ዳኞች የእውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡ Read more
ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮሮና ቫይረስ... ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮሮና ቫይረስ... Tuesday, October 27, 2020 3654 ጥቅምት 5/2013 ዓ.ም የኢትጵያ የሕግ ባለሞያዎች ማህበር ለፌ/መ/ደ/ፈ/ቤት ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያስችል የተለያዩ የጥንቃቄ ግብአቶች (Personal Protective Equipment) በድጋፍ መልኩ አበርክቷል፡፡ Read more
ፍርድ ቤቶች የሕዝብ አመኔታ እንዲያገኙ ዳኞች በዘርፉ ላሉ... ፍርድ ቤቶች የሕዝብ አመኔታ እንዲያገኙ ዳኞች በዘርፉ ላሉ... Tuesday, October 27, 2020 3611 የፌደራል ፍርድ ቤቶች በአገልግሎት አሰጣጣቸው የሕዝብ አመኔታ ሊያተርፉ የሚችሉት ሥራቸውን የዳኝነት የሥነምግባር ደንቡን እና ዓለም አቀፍ የዳኝነት የሥነምግባር መርሆዎችን መሠረት አድርገው ሲያከናውኑ መሆኑ ተገለጸ፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more