Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ሳሙኤል ድረስ ደመቀ እና ዳሽን ባንክ አ.ማ የሰ/መ/ቁ 259234

ጉዳዩ የስራ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡በስር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡

አመልካች መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በተጻፈ ክስ በተጠሪ ባንክ ዉስጥ በምክትል ሥራ አስኪያጂነት የስራ መደብ ከሚያዝያ 24 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በራሴ ፍቃድ የስራ ዉሉን እስካቋረጥኩበት ታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጠቅላላ ብር 46,191.01(አርባ ስድስት ሺ አንድ መቶ ዘጠና አንድ ከ01/100) እየተከፈለኝ በቋሚነት ተቀጥሬ እሰራ የነበረ ሲሆን ስራዉን በገዛ ፍቃዴ ስለቅ ተጠሪ ሊከፍለኝ የሚገባዉን የተጠራቀመ ፕሮፊደንት ፈንድ፣ የአገልግሎት ክፍያ፣ የተጠራቀመ የአመት ፍቃድ፣ ጠቅላላ ብር 541,422.78(አምስት መቶ አርባ አንድ ሺ አራት መቶ ሃያ ሁለት ከ78/100) ሊከፍለኝ ስላልቻል ይህን ክፍያ እንዲከፍለኝ እንዲሁም ክፍያዉ ለዘገየበት የካሳ ክፍያ፣ ያለስራ ለተቀመጥኩበት የሶስት ወር ደመወዝ ካሳ እና የስራ ልምድ ከእዳ ነፃ ተብሎ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…    

Previous Article አቶ መንገሻ መሮ እና እነ መ/ር መስፍን መንገሻ (2ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 258429
Next Article አቶ አሸናፊ ተስፋዬ እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የሰ/መ/ቁ 259817
Print
5297

Documents to download

  • 259234(.pdf, 852.85 KB) - 649 download(s)

«July 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
293012345
6789101112
13141516171819
20212223242526
272829303112
3456789

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ 2018 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቅ...

1543

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2018 የመጀመሪያዉ መንፈቅ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የውይይት መድረክ የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳኞች እና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ተደርጓል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል...

947

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደዉ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንቶችን እና 50 የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የ2018...

1377

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 2018 በጀት ዓመት የመንፈቅ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ በቀን 27/2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የሶስቱም ፍርድ ቤቶች አመራሮችና የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

የፌዴራል መንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ...

1289

ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ 1333/2016፣ መመሪያዎች እና ኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዥ አጻጸም (e-GP) ስርዓት ክህሎት ላይ ከጥር 21 እስከ 23/2018 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡

First45679111213Last