Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ጉዕሽ ካሳ ደሞዝ እና እነ አቶ አማኑኤል ወልደሊባኖስ ተስፋዬ የሠ/መ/ቁጥር 243564

ጉዳዩ ዳግም ዳኝነት የሚታይበትን አግባብ የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው አመልካች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የዳግም ዳኝነት አቤቱታ በማቅረባቸው ሲሆን ችሎቱ ክርክሩን መርምሮ ለሰጠዉ ዉሳኔ መነሻ ያደረገዉ ተጠሪዎች ለስር ፍርድ ቤት ያቀረቡትን የሰነድ ማስረጃዎች መሆኑን፤ነገር ግን የኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ለአመልካች ድርጅት ብር 17,500,000.00 መክፈሉን ለማረጋገጥ በይግባኝ ሰሚዉ ችሎት በመ/ቁጥር 211132 እና በመ/ቁጥር 211227 ላይ ይግባኝ ያቀረቡት የአሁን ተጠሪዎች ለስ ፍርድ ቤት በማስረጃነት ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃ ሐሰተኛ ስለመሆኑ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 249579 ላይ በቀን 16/10/2014 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ማረጋገጡን በመዘርዝር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥርር 6 መሠረት ዳግም ዳኝነት እንዲታይላቸዉ ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሰ.መ.ቁ 246233
Next Article እነ አቶ አበራ ነጋሽ ደምሴ(6) ሰዎች እና ቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኔዓለም ቤ/ክርስቲያን፤ የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት የሰበር መ/ቁ/245981
Print
5215

Documents to download

  • 243564(.pdf, 1.07 MB) - 687 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ፤ ለሀገረ መንግስት...

986

የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ''የዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት እምርታ ለተሳካ ሀገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በዳኝነትና የዴሞክራሲ ተቋማት የለውጥ ስራዎች ላይ በማተኮር ሲካሄድ የቆየው የምክክር መድረክ ተጠናቋል።

ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ...

1048

ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ቅሬታዎች እና አፈታት ላይ ለፌዴራል እና ለክልል ዳኞች ከቀን 09/06/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ3 ዙር ለ9 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በቀን18/5/2018 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡

በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ ለፌዴራል ጠቅላይ እና...

1151

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዳኒሽ ኢንቲትዩት ፎር ሁማን ራይትስ ጋር በመተባበር ከፌዴራል ጠቅላይ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተውጣጡ ዳኞች በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ በስድስት የስልጠና ርእሶች በተከታታይነት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና የማጠናቀቂያ መርሐግብር የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሂዷል።

አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ...

1566

አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ ጸሐፊ II በ ቀን 06 እና 09/06/2018 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታን እና ከለዉጥ ስራዎች ጋር ለማስተዋወቅ የመግቢያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

First45679111213Last