Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056 ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በወረዳዉ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ የአመልካች አዉራሽ ሟች አቶ ይልማ ወልደአብና ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር ላይ በተጠቀሱት ተጠሪዎችና በአመልካች አባት በሟች አቶ ይልማ ወልደአብ ላይ ባቀረቡት ክስ በክሱ ላይ አዋሳኞቹ የተመለከተዉን 400 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈዉን የመኖሪያ ቤት ከነሰርቪስ ቤቶቹ ጭምር የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ/ም በተፈረመ የሽያጭ ዉል ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች (ከሥር 1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች) በብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ገዝተዉ ካርታ በስማቸዉ የተሰጣቸዉ ቢሆንም በይዞታዉ ላይ ካሉ ቤቶች መካከል አንዱን የአመልካች ወላጅ አባት (የሥር 4ኛ ተከሳሽ) ይዘዉ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸዉን ገልፀዉ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተጠሪዎች (የሥር 1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች) የሸጡላቸዉን ቤት ከአመልካች አባት (የሥር 4ኛ ተከሳሽ) አስለቅቀዉ እንዲያስረክቡና የአመልካች አባትም (የሥር 4ኛ ተከሳሽም) መብት ሳይኖራቸዉ የያዙትን የ1ኛ ተጠሪን (የሥር ከሳሽን) ቤት ለቀዉ እንዲወጡ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት በመጠየቅ ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article የፌደራል ዐቃቤ ህግ እና አቶ አበበ ወንድሙ ኤጋ የሰ/መ/ቁጥር 251759 Next Article የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አቶ መጣልኝ መላኩ የሰ.መ.ቁ.252953 Print 2670 Documents to download 252056(.pdf, 838.15 KB) - 341 download(s)
18ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በፌደራል ጠቅላይ... 18ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በፌደራል ጠቅላይ... Monday, October 13, 2025 746 በአገር አቀፍ ደረጃ "ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!" በሚል መሪ ቃል 18ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ሥነሥርዓት ተከብሯል፡፡ Read more
ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ Monday, October 13, 2025 934 ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች "Building the power of trust and enhancing judicial integrity" እና "The role of technology in building judicial trust and enhancing accessibility" በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከቀን 01-02/02/2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የቆየ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ Read more
የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ... የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ... Monday, October 13, 2025 799 የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ፣የፌደራል ፍርድ ቤት አመራሮች፣ክቡራን ዳኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂደል፡፡ Read more
በሶማሌ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት... በሶማሌ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት... Tuesday, September 9, 2025 716 ልዑክ ቡድኑ በነበረው ቆይታም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተከናወኑ ያሉ በርካታ የለውጥ ተግባራትና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት አፈጻጸሞች እንዲሁም አተገባበር ምን እንደሚመስል በቀን 04/13/2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ምልከታ እና ውይይት አካሂዷል ፡፡ Read more
12Dec2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Friday, December 12, 2025 Read more
6Nov2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Thursday, November 6, 2025 Read more
8Oct2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Wednesday, October 8, 2025 Read more