Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947 ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ… Previous Article ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243 Next Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Print 5515 Documents to download 259947(.pdf, 828.26 KB) - 696 download(s)
የፌደራል ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የ2018... የፌደራል ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የ2018... Monday, February 9, 2026 957 የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት 2018 በጀት ዓመት የመንፈቅ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ በቀን 27/2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የሶስቱም ፍርድ ቤቶች አመራሮችና የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ Read more
የፌዴራል መንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ... የፌዴራል መንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ... Monday, February 9, 2026 928 ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ 1333/2016፣ መመሪያዎች እና ኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዥ አጻጸም (e-GP) ስርዓት ክህሎት ላይ ከጥር 21 እስከ 23/2018 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡ Read more
ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሬጂስራርና ችሎት አገልግሎት... ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሬጂስራርና ችሎት አገልግሎት... Monday, February 9, 2026 597 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሬጂስትራርና ችሎት አገልግሎት ክፍል ለተውጣጡ ሰራተኞች በሙስና ምንነት፣ በሙስና ባህሪያት፣ በአዋጅ 881/2007 የተደነገጉ የሙስና ወንጀሎች፣ የሙስና መከላከያ ስልቶች እና በሥነ ምግባር ፅንሰ ሃሳብ ዙሪያ በቀን 23/5/2018 ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል:: Read more
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር አመራሮች በፌደራል... የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር አመራሮች በፌደራል... Thursday, January 29, 2026 591 የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር አመራሮች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 20/05/2018 ዓ.ም በመገኘት ወደፊት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more