Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 Print 9479 Documents to download 266395(.pdf, 849.74 KB) - 1118 download(s)
የተማሪዎችን የሕግ ግንዛቤ ለማሳደግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ የተማሪዎችን የሕግ ግንዛቤ ለማሳደግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ Sunday, May 16, 2021 5246 በትምህርት ቤቶችና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ያላቸውን የሕግ ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በትምሕርት ሚኒስቴር፣ በሳይንስና ከፍተኛ ትምሕርት ሚኒስቴር እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት መካከል ተፈረመ፡፡ Read more
ለስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት የተካሄዱ የትንተና ጥናቶች... ለስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት የተካሄዱ የትንተና ጥናቶች... Saturday, May 8, 2021 4673 በአማካሪ ድርጅት የሚሰራውን ሶስተኛው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት ሂደትን እንዲከታተል በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተቋቋመው ዓብይና የቴክኒክ ኮሚቴ አማካሪ ድርጅቱ ለስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት ባካሄዳቸው የትንተና ጥናቶች ላይ ተጨማሪ ግብዓት ሰጠ፡፡ Read more
ፍርድ ቤቶች በዘጠኝ ወሩ ከአንድ መቶ 19 ሺህ በላይ... ፍርድ ቤቶች በዘጠኝ ወሩ ከአንድ መቶ 19 ሺህ በላይ... Friday, May 7, 2021 5265 የፌደራል ፍርድ ቤቶች በ2013 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ለ119, 413 መዛግብት እልባት መስጠታቸውን የሶስቱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተጠቃለለ የዘጠኝ ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አመለከተ፡፡ Read more
ፍርድ ቤቱ በአገልግሎት አሰጣጥ መልካም ተሞክሮ ለመቅሰም... ፍርድ ቤቱ በአገልግሎት አሰጣጥ መልካም ተሞክሮ ለመቅሰም... Thursday, April 29, 2021 4714 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሬጂስትራር አገልግሎትን ለማሻሻል የሚያስችለውን መልካም ተሞክሮ ለመቅሰም በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉብኝት አደረገ፡፡ Read more
8Oct2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Thursday, October 8, 2026 Read more