Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ አየለ ሽፈራው እና ጎባ ወረዳ ፍ/ቤት ጎባ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ. 255190

ጉዳዩ የመንግሥት ሠራተኛን ከሥራና ከደመወዝ ማገድ ሕጋዊነትን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የደ/ም/ኢት/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ይግባኝ ባይ ሲሆን ተጠሪዎች መልስ ሰጪዎች ነበሩ፡፡ ተጠሪ በ22/03/2015 ዓ/ም ለአስተዳደር ፍ/ቤት ጽፈው ባቀረቡት የይግባኝ ቅሬታ ተጠሪዎች የትምህርት ማስረጃዬ ሀሰተኛ ስለመሆኑ ባላረጋገጡበት ዲፕሎማ ሰርተፍኬትህ ሀሰተኛ ነው በማለት ከስራ እና ደመወዝ ያለአግባብ ያገዱኝ ስለሆነ ወር ደመወዜ ከተቋረጠበት ከጥቅምት 1 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ ተከፍሎኝ ወደ ሥራ እንድመለስ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

Previous Article የአቶ ፍስሃ ወ/ገሪማ እና የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሰ/መ/ቁ. 253575
Next Article ወ/ሮ የሺ ሽብሩ እና አቶ ከበደ ድንቁ የሰበር መ/ቁ255586
Print
5088

Documents to download

  • 255190(.pdf, 863.92 KB) - 560 download(s)

«September 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
31123456
78910111213
14151617181920
21222324252627
2829301234
567891011

ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ስርዓትን ለማስፈን ያለመ...

34

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት፤ ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ሂደት ትግበራን በተመለከተ ለመርማሪ ፖሊስ አባላት እና ለክቡራን ዳኞች በሁለት ዙር የተከፈለ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ...

77

ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሠራተኞችን መብት፣ ግዴታና የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮችን በማካሄድ ተጠናቋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ...

116

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሰራተኞች መድረክ በዛሬው ዕለት መካሄድ የጀመረ ሲሆን የፍርድ ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዷል።

1345678910Last