Selam Warga / Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation እነ አቶ ዮሐንስ ገ/ሚካኤል(5ሰዎች) እና ወ/ሮ ሃና ደርሶልኝ(2ሰዎች) የሰበር መዝገብ ቁጥር - 256463 አመልካቾች ሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም በተፃፈ የመቃወም አቤቱታ ሟች አባታቸው አቶ ገ/ሚካኤል ኃ/ማርያም በህይወት እያሉ እንዲሁም አባታቸው ከሞቱ በኃላ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ የሆኑት፣ አመልካቾችና የ 96 አመት የሆኑት የግራ ቀኙ እናት ጋር በአልኮልና በለስላሳ ማከፋፈያ እንዲሁም በሸቀጣሸቀጦች ጅምላ ንግድ ስራ ተሰማርተው በቁጥር ስምንት የሆኑ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች፤ ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ሆቴል፣ የቡና ማበጠሪያ፣ የመጠጥ ማከፋፈያ፣ የመኖሪያ ቤትና መጋዘን፤ በቡና ግብይት ላይ የነበረ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ብር፣ በአዋሽ ባንክ ያለ 50 የአክስዮን ድርሻ በጋራ ያፈሩ መሆኑንና ተጠሪዎች ጋብቻ ሲፈፅሙ እነዚህ ንብረቶች የአመልካቾች መሆናቸውን በጋብቻ ውላቸው ተስማምተዋል፡፡ እነዚህ ንብረቶች ከፊሎቹ ባሉበት ከፊሎቹ በሽያጭ ሆነ በሌላ መንገድ እየተለዋወጡና እየተቀላቀሉ ብዛታቸው 16 የሆኑ በተጠሪ ስም የተመዘገቡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፤ በተጠሪ ስም የተመዘገቡ በአዋሽ ባንክ፣ በኦሮሚያ ባንክ፣ በህብረት ባንክ ያሉ አክስዮኖች፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በአዋሽ ባንክ፣ በህብረት ባንክ፣ በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፣ በኦሮሚያ ባንክ ተጠራቅሞ የሚገኝ ገንዘብ እና ተሸከርካሪዎች በቤተሰብ የተፈሩና በተጠሪዎች የጋብቻ ውል ላይም የቤተሰብ ንብረቶች መሆናቸው ተረጋግጦ እያለ ተጠሪዎች ከዚህ በተቃራኒ በሰበታ ከተማ የሚገኘውን በ 612 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ቤት፣ በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት እንዲሁም በዚህ ከተማ በ 2,000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሆቴል ን በመተው ሌሎችን ንብረቶች የተጠሪዎች የጋራ ንብረት ነው በማለት ያስወሰኑ በመሆኑ ውሳኔው ቀሪ እንዲሆን በማለት የመቃወም አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ… Previous Article ቻይና ኮሙኒኬሽን ኩባንያ ግንባታ ወንጪ ደንዲ ኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት እና ማንዴሳ ጪብሳ የሠ/መ/ቁጥር 256412 Next Article ወ/ሮ ሰላማዊት ያደሳ እነ አቶ ፀሀዬ ጌታቸው(2ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 256923 Print 5586 Documents to download 256463(.pdf, 853.95 KB) - 566 download(s)
"የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... "የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ፕሮጀክት የፍርድ ቤቶችን... Friday, July 17, 2026 0 የዳኝነት ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ ላለፋት ዓመታት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ላይ ሲተገብር የቆየው የቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያተኮረው የዋይድ ኤርያ ኔትወርክ ፕሮጀክት (Wide Area Network Project) የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ... Tuesday, June 30, 2026 289 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር የተቀናጀ አሰራርን በመፍጠር የዳኝነት ስርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል። Read more
ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... ለበጎ ፈቃደኛ ጠበቆችና የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል... Monday, June 29, 2026 283 በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች፣ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እና ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አስተባባሪዎች የልምድ ልውውጥና ተግባር ተኮር የዉይይት ተካሂዷል። Read more
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ... Monday, June 8, 2026 408 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል። Read more
10Mar2026 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Tuesday, March 10, 2026 Read more