Selam Warga / Tuesday, June 17, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰበር መዝገብ ቁጥር 266395 ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው 1ኛ ክስ የወ/ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 34(1) እና 693(1) በመተላለፍ በትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ውስጥ የፋብሪካው ኃላፊ እና ባለንብረት ሆኖ በሚሰሩበት ጊዜ ለግል ተበዳይ አቶ ሸምሱ አወል የብር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚመነዘር ቼክ ሰጥቶ የግል ተበዳይ ገንዘቡን ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄድ በቂ ገንዘብ የለውም በመባሉ ገንዘቡን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በመስጠት ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡ አመልካች የወንጀሉን ድርጊት አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ በመከራከሩ ተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ እንደ ክስ አቀራረቡ አስረድቷል፡፡ አመልካች እንዲከላከል ታዞ መከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን የአመልካች መከላከያ ምስክሮች ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቼክ መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Previous Article ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 Next Article ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 267231፣267230 Print 3674 Documents to download 266395(.pdf, 849.74 KB) - 582 download(s)
በአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋዩች አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ በአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋዩች አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ Tuesday, January 13, 2026 7 ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰው ሃብት ስራ አመራር ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች፣ በሬጅስትራር ስር ላሉ እና ለሌሎች የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም በአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋዩች አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡ Read more
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በወንጀል ችሎት በሚታዩ ችግሮችና... በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በወንጀል ችሎት በሚታዩ ችግሮችና... Tuesday, January 13, 2026 2 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በወንጀል ችሎቶች የሚታዩ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች ዙሪያ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ላይ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም የግብዓት ማሰባሰቢያ ዉይይት ተካሄዷል፡፡ Read more
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል... የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል... Tuesday, January 13, 2026 1 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደዉ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 81(2) መሰረት 34 የከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፡፡ Read more
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል... የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል... Tuesday, January 13, 2026 1 የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከቀን 21/04/2018 ዓ.ም እስከ 27/04/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት ጉብኝት እና ውይይት አድርገዋል፡፡ Read more
12Dec2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Friday, December 12, 2025 Read more
6Nov2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Thursday, November 6, 2025 Read more
8Oct2025 በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት ውስጥ ሚገኝ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ Wednesday, October 8, 2025 Read more