Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መንገሻ መሮ እና እነ መ/ር መስፍን መንገሻ (2ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 258429

በአመልካቾች የይግባኝ አቤቱታው የቀረበለት የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ተጠሪዎች ከወላጆቻቸው ይዞታ በመውሰድ በራሳቸው ጉልበት እና ገንዘብ ያለሙ እና ለምርትም ሲደርስ ለአመልካች እና ባለቤታቸው እኩል በማካፈል በጋራ ሲጠቀሙ የነበሩ በመሆናቸው እንዲሁም የቤተሰብ አባል በመሆን በቤተሰብ በተመዘገበ ይዞታ ላይ እየተጠቀሙ የነበሩ በመሆናቸው የመጠቀም መብታቸው ቀሪ ሊሆን እና ያፈሩትንም ንብረት ሊያጡ አይገባም፣የስር ፍ/ቤቶችም ተጠሪዎች በይዞታው ላይ መብት የላቸውም በማለት የሰጡት ውሳኔ ተጠሪዎች በይዞታው ላይ ካላቸው መብት እና የቤተሰብ አባልነት አኳያ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውም ይዞታው ላይ የሚገኝ ቡና እና ኮረሪማ ባልና ሚስቱ ሊካፈሉ አይገባም፣አመልካች እና ባለቤታቸው ከተጠሪዎች ጋር በጋራ ሊጠቀሙ ይገባል በሚል ወስኗል፡፡ አመልካችም የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በሚል ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡ ሲሆን አቤቱታው የቀረበለት ችሎትም ውሳኔው የህግ ስህተት አልተፈጸመበትም በማለት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡

አመልካችም ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ በአጭሩ ተጠሪዎች በውል ወይንም በውርስ ያገኙት የይዞታ ባለቤትነት መብት ሳይኖራቸው መከራከራቸው በህገ መንግስት አንቀጽ 40/7/8 የተቀመጠውን መብት ጥሰት ነው፡፡ተጠሪዎች መሬቱን ከ2000 ዓ.ም ጀምረው አልምተውታል ቢባል እንኳን አባታቸውን ስላገዙ የባለቤትነት መብት አይሰጣቸውም፡፡የክርክር መነሻ የሆነውን ይዞታ ያገኘሁት በአዋጅ ቁጥር 110/99 መሰረት አርሶአደር በመሆኔ ሲሆን ተጠሪዎች የከተማ ነዋሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞች በመሆናቸው በውርስም ከሆነ ከሞትኩ በኃላ የሚፈፀም ይሆናል እንጂ በህይወት እያለው ይዞታውንና ንብረቱን ሊካፈሉ አይችሉም በሚል የተሰጠው ውሳኔ እንዲታረም ጠይቀዋል፡፡  መልካም ንባብ…

Previous Article እነ ወ/ሮ ተናኜ ሞላ ብርሐኔ(3ሰዎች) እና አቶ ሳሙኤል ተገኝ ኃይሌ የሰበር መዝገብ ቁጥር - 257774
Next Article አቶ ሳሙኤል ድረስ ደመቀ እና ዳሽን ባንክ አ.ማ የሰ/መ/ቁ 259234
Print
5607

Documents to download

  • 258429(.pdf, 1.07 MB) - 676 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

‎በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል...

23

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል የተዘረጉትን የኢ-ፋይሊንግ፣ የትራንስክሪፕሽን እና የርቀት ችሎት አገልግሎቶችን በአካል ተገኝተው አስመርቀዋል።

የፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ...

0

ነሐሴ 03/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ የፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች ልዑክ በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ ተካሄደ

26

ፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የጉባኤው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመክፈቻ ንግግራቸው፤ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሠረት የተቋቋመው የፌደራል ጉባኤ የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን የመጠበቅ፣ የአሰራር መመሪያዎችን የማውጣትና የማሻሻል እንዲሁም አገራዊ የዳኝነት ሂደቱን የማጠናከር ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

1345678910Last