Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ኃይሉ እና እነ ወ/ሮ እታገኘው ኃይሉ(4ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 253718

ጉዳዩ የውርስ ማጣራትን ተከትሎ የውርስ ሀብት ስለመሆኑ በተለየ ንብረት ላይ መብት ያላቸው ወራሾች ሊያገኙ ይችሉ የነበረውን ገቢ ቤቱን ከያዘው ሰው ለመጠየቅ ያላቸውን መብት የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን 1ኛ፣2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ከሳሾች፣4ኛተጠሪ ጣልቃገብ አንደዚሁም አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡በተጠሪዎች የቀረበው ክስ በአጭሩ ሟቾች አቶ ሀይሉ ደነቀው እና ወ/ሮ ልንገርሽ ይሁኔ በ422 ካ.ሜ ላይ ያረፈና የቤት ቁጥር 191 የሆነ ዋና ቤትና ሰርቪስ ቤቶች የነበሯቸው ሲሆን በመ/ቁ 82464 በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት በነበረን የውርስ ሀብት ይጣራልን ክርክር ላይ የሟች አቶ ኃይሉ ደነቀው የውርስ ሀብት ተጣርቶ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡አመልካች በኑዛዜ የተላለፈላቸው 02 ክፍል ቤት ብቻ ሲሆን ክፍሎቹን እያከራዩ የሚጠቀሙበት ሆኖ በውርስ የሚደርሰንን ዋና ቤትና ሰርቪስ ቤቶችን ከህግ አግባብ ውጪ በመያዝ በዋናው ቤት እየኖሩበት አከራይተን እንዳንጠቀም በማድረግ ሰርቪስ ቤቶቹን ከተከራዩት ሰዎች ላይ የኪራዩን ገንዘብ በመሰብሰብ ለራሳቸው ጥቅም በማዋል ልናገኝ የሚገባውን ጥቅም አሳጥተውናል፡፡በመሆኑም በውሳኔው መሰረት የሚኖሩበትን ዋናውን ባለ ሶስት ክፍሉን ቤት እና የምያከራዩትን 03 ክፍል ሰርቪስ ቤቶች ከነቦታው ለቀው እንዲያስረክቡን በተደጋጋሚ ከመጠየቅ ባሻገር ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ደግሞ የጹሑፍ ማስጠንቀቂያ የሰጠናቸው ቢሆንም አመልካች ቤቶቹን ለማስረከብ እንደዚሁም የቤቶቹ ኪራይ ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሟች ከሞቱበት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ዋናው ቤት ቢከራይ በወር ብር 8000 (ስምንት ሺህ) ክስ እስካቀረብንበት ጊዜ ድረሰ ያለውን የ28 ወር ብር 224,000.00 (ሁለት መቶ ሀያ አራት ሺህ) እንዲከፍሉን፣የሚከራዩ 3 (ሶስት) ክፍል ሰርቪስ ቤቶች ሟች ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ ወር ብር 1500 (አንድ ሺ አምስት መቶ) ይከራይ የነበረው አመልካች ብር 300 (ሶስት መቶ) በመጨመር ብር 1800 (አንድ ሺ ስምንት መቶ)፣ ሌላው 1 (አንድ) ክፍል ቤት 500 (አምስት መቶ) ይከራይ ነበረው ብር 700 (ሰባት መቶ) እና ቀሪውን 01 ክፍል ቤት በብር 1000 (አንድ ሺህ) ልዩነቱ የ4 (አራት) ወር ብር 4000 (አራት ሺ)  ሟች ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መጋቢት ወር መጨረሻ ክስ እስካቀረብንበት ጊዜ ድረስ ያለው ሲሰላ ሁለት ዓመት 24 (ሀያ አራት) ወር በመሆኑ ብር 70,000.00 (ሰባ ሺህ) በድምሩ ብር 74,000 (ሰባ አራት ሺህ) ልናገኝ የሚገባውን ጥቅም ያሳጡን ስለሆነ ዋናውን ቤት እና የሰርቪስ ቤቶቹን የኪራይ ገንዘብ ተከፍሎ እስከሚጠናቀቅበት ድረስ ከነወለዱ ታስቦ እንድከፍሉን እንዲወሰንልን የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…..

Previous Article ሐረማያ ዩንቨርስቲ እና መላ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግል ማሕበር የሰ/መ/ቁ. 253530
Next Article ወ/ሮ ሳፊያ ከድር እና እነ ሐጂ አማን ሐጂ ሁሴን (6ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 254696
Print
5467

Documents to download

  • 253718(.pdf, 1.07 MB) - 694 download(s)

«August 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

‎በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል...

23

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአርባ ምንጭ ማዕከል የተዘረጉትን የኢ-ፋይሊንግ፣ የትራንስክሪፕሽን እና የርቀት ችሎት አገልግሎቶችን በአካል ተገኝተው አስመርቀዋል።

የፍርድ ቤቶች አመራሮችና ዳኞች በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ...

0

ነሐሴ 03/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ የፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮችና ዳኞች ልዑክ በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ ተካሄደ

26

ፌደራል ፍርድ ቤቶች ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የጉባኤው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመክፈቻ ንግግራቸው፤ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 መሠረት የተቋቋመው የፌደራል ጉባኤ የዳኝነት ነፃነትና ገለልተኝነትን የመጠበቅ፣ የአሰራር መመሪያዎችን የማውጣትና የማሻሻል እንዲሁም አገራዊ የዳኝነት ሂደቱን የማጠናከር ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

1345678910Last