Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ሲሲኢሲሲ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ እና አቶ ቤልሻጽር ሀይለልዑል መ/ጽድቅ የሰ.መ.ቁ.250942

ይህ የስራ ስንብት ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ሰበር ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.296508 በ29/10/2015 ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከቱ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበዉ የክስ አቤቱታ፡ አመልካች በተጠሪ ድርጅት በብሮ ስራ መሃንዲስ የሥራ መደብ ተቀጥሬ በወር 80,000 (ሰማንያ ሺህ) እየተከፈለኝ በአርሲ ሮቤ ዋቤ ሪቨር ፕሮጀክት ሲሰራ የቆየሁ ሲሆን ተጠሪ በ02/12/2014 ዓ.ም በሕገወጥ መንገድ ከሥራዬ ስላሰናበተኝ ተገቢ ክፍያዎችን እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መለካም ንባብ….

Previous Article እነ አቢብ አብዲ (3) ሰዎች እነ ዓሊ ዮሜ ዩሱፍ የሰ/መ/ቁጥር---250757
Next Article ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ እና ኤም.ኢ.ኤስ.ፒ. አፍሪካ ኃ.የተ.የግ. ማህበር ፤የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት የሠ/መ/ቁጥር 251398
Print
2858

Documents to download

  • 250942(.pdf, 865.73 KB) - 432 download(s)

«January 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
2930311234
567891011
12131415161718
19202122232425
2627282930311
2345678

በአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋዩች አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ

14

ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰው ሃብት ስራ አመራር ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች፣ በሬጅስትራር ስር ላሉ እና ለሌሎች የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም በአገልግሎት አሰጣጥና የተገልጋዩች አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በወንጀል ችሎት በሚታዩ ችግሮችና...

5

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በወንጀል ችሎቶች የሚታዩ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች ዙሪያ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ላይ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም የግብዓት ማሰባሰቢያ ዉይይት ተካሄዷል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል...

2

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደዉ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 81(2) መሰረት 34 የከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፡፡

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል...

3

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከቀን 21/04/2018 ዓ.ም እስከ 27/04/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት ጉብኝት እና ውይይት አድርገዋል፡፡

245678910Last