Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

የፌደራል ዐቃቤ ህግ እና አቶ አበበ ወንድሙ ኤጋ የሰ/መ/ቁጥር 251759

አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተጠሪ የወ/ህ/ቁ.539(1)(ሀ) ን ተላልፈው ሰው ለመግደል አስቀድሞ በነበረው ሀሳብ ጨካኝነቱንና ነውረኝነቱን በሚያሳይ ሁኔታ ወንድሙን ሟች ጀንበሩ ወንድሙን ከአሁን በፊት ሰድቦኛል እንዲሁም በሚያሽከረክረው መኪና ሊገጨኝ ሞክሯል በማለት በቂም በቀል በመነሳት ሽጉጥ ተኩሶ ማጅራቱን ሲመታው ሲወድቅ በተደጋጋሚ ሶስት ጊዜ ተኩሶ ግንባሩን በቀኝ በኩል አንገቱንና በግራ በኩል አንገቱን በመምታት የጥይት እርሳስ ጉዳት በራስ ቅሉ የኋለኛው ክፍል፤የክብ ቅርፅ ያለው ጥይት እርሳስ የገባበት ቁስል በራስ ቅሉ የኋለኛው ክፍል፤ሳተላይት ቅርጽ ያለው የጥይት እርሳስ የወጣበት ቁስል፤በግራ ግንባሩ የፊተኛው ክፍል ላይ የአጥንት መሰበር ጉዳት፤በራስ ቅሉ ፊተኛው የታችኛው ክፍል ላይ እንዲደርስበት፤የመበሳት ጉዳት በአንገቱ ላይ እንዲደርስበት ፤በአንጎሉ የላይኛው ሽፋን ክፍል የተሰራጨ የደም መፍሰስ እንዲሁም የአየር ባንቧው የመበለዝ ጉዳት እና በዙሪያው ከፍተኛ ደረጃ ያለው የውስጥ ደም መፍሰስ ጉዳት እንዲደርሰበት እና ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓ በዚህም ከባድ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ፈፅሟል በማለት ከሷል፡፡መልካም ንባብ….

Previous Article ህብረት ኢንሹራንስ አ.ማ እና ኤም.ኢ.ኤስ.ፒ. አፍሪካ ኃ.የተ.የግ. ማህበር ፤የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጀት የሠ/መ/ቁጥር 251398
Next Article አቶ ኃይለ ጊዮርግስ ይልማ ወልደአብ እና እነ አቶ አዲስ እሸቱ (4) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 252056
Print
4634

Documents to download

  • 251759(.docx, 142.83 KB) - 578 download(s)

«June 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
25262728293031
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293012345

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ...

0

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል።

ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ...

33

‎በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።

ለሶሻል ወርክ ባለሞያዎች በተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል ረቂቅ...

60

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በፍትህ ስርዓት ውስጥ የሚያገለግሉ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎችን ሚና ለማጎልበት የሚያግዝ የስልጠና ማንዋል የመጨረሻ ረቂቅ ሰነድ ላይ የውይይት እና የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል፡፡ 

‎የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን...

58

በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት በክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አጠናቋል።

245678910Last