Selam Warga
/ Categories: CASSATION, Cassation

ሐረማያ ዩንቨርስቲ እና መላ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግል ማሕበር የሰ/መ/ቁ. 253530

ጉዳዩ ከግንባታ ውል ጋር በተያያዘ በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ በቀረበው የዳኝነት ጥያቄ መሰረት መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበርአቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ተከሳሽ ነበር፡፡አመልካች በ20/01/2013 ዓ/ም ጽፎ ባቀረበው ክስ አመልካች እና ተጠሪ በነሀሴ 2009ዓ/ም እ.ኤ.አ የማስፋፊያ ግንባታ ለማከናወን ተስማምተው ተጠሪ ሳይቱን በመረከብ የግንባታ ማስፋፊያ ስራውን ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በውሉ በተቀመጠው ጊዜ እና ጥራት የግንባታ ስራውን ማከናወን ባለመቻሉ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቅያ ሰጥቶ ስራው 93% ላይ እያለ አመልካች ውሉን አቋርጧል፡፡ በመሆኑም ለአምስት ሕንፃዎች/ብሎኮች የስራ ግድፈት ማስተካከያ ብር 2,031,357.91፣ ለኩሽና፣ መጽሀፍት ቤትና ምግብ ቤት ማስተካከያ ሥራ ብር 350,759.30፣ የውሉ አፈጻጸም በመዝግየቱ በውሉ አንቀጽ 49.1 መሰረት የጠቅላላ ውሉን ዋጋ 10% የደረሰ ኪሣራ ብር 5,219,807.91እና የቀሪ ሥራ ማጠናቀቂያ ብር 492,255.18በድምሩ ብር 10,107,964.5 ተጠሪ እንዲከፍል እንዲወሰንለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…..

Previous Article አቶ ቴዎድሮስ መስፋን ህንፃ ሥራ ተቋራጭእና አዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (በአሁኑ - የአ/አ ቤ/ልማት ኮርፖሬሽን) የሰበር መ/ቁ 253303
Next Article ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ኃይሉ እና እነ ወ/ሮ እታገኘው ኃይሉ(4ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 253718
Print
5790

Documents to download

  • 253530(.pdf, 849.38 KB) - 731 download(s)

«September 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
31123456
78910111213
14151617181920
21222324252627
2829301234
567891011

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ...

47

ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሠራተኞችን መብት፣ ግዴታና የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮችን በማካሄድ ተጠናቋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ...

41

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሰራተኞች መድረክ በዛሬው ዕለት መካሄድ የጀመረ ሲሆን የፍርድ ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዷል።

1345678910Last