Selam Warga / Thursday, June 5, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሰ.መ.ቁ 246233 የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ለግልግል ዳኝነት ጉባኤ በ1ኛ አመልካች ላይ ባቀረበው ክስ በተጠሪ እና በ2ኛ አመልካች(ስር ጣልቃገብ ) መካከል ከወራቤ እስከ በጆበር ያለውን 38.5ኪ.ሜ የመንገድ ስራ ፐሮጀክት ለማከናወን እ.ኤ.አ ሜይ 20 2016 ውል የተፈረመ ሲሆን የውሉም አይነት ስራ ተቋራጩ(2ኛ አመልካች) የዲዛይንና የግንባታ ስራውን በሙሉ በኃላፊነት የሚያከናውንበት ነው፡፡ በውሉ መሰረት ስራ ተቋራጩ የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና የማቅረብ ግዴታ ስላለበት ይህን ተከትሎ ተቋራጩ የውሉን 10% ይኅውም ለብር 45‚844‚565 እ.ኤ.አ ከሜይ 13 2016 ጀምሮ ለአራት አመት ጸንቶ የሚቆይ የቦንድ ፖሊሲ ቁጥሩ በተገለጸ 1ኛ አመልካች የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ሰጥቷል፡፡ በውሉ መሰረት እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 26 2017 የተጀመረው የግንባታ ስራ በ1095 ቀናት ተጠናቆ ለግዜያዊ ርክክብ ብቁ መደረግ ሲገባው እና ከአመት በኋላ ጃንዋሪ 2018 አፈጻጸሙ 30.38% መሆን ሲገባው የስራ ተቋራጩ አፈጻጸም የውሉ 8% ላይ ነበር፡፡ በዛን ግዜም ከውሉ መፈጸሚያ ግዜ 33.8% ባክኖ ነበር፡፡ ተጠሪ ለስራ ተቋራጩ በቂ የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ቢሰጠውም፤ ሶስት የክፍያ ሰርተፍኬቶችም ጸድቀው ገንዘብ ቢከፈለውም፤ የውል ግዴታውን እንዲወጣ ተጠሪና የፕሮጀክቱ አማካሪ ድርጅት ተደጋጋሚ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ ቢሰጡትም ይህን ባለመቀበል የግንባታ ቦታውን ጥሎ በመሄድ አይነተኛና መሰረታዊ የውል ጥሰት በመፈጸሙ ተጠሪ በውሉ መሰረት እ.ኤ.አ በ1/3/18 በተጻፈ ደብዳቤ የ2ኛ አመልካችን(ስራ ተቋራጭ) የስራ ውል አቋርጧል፡፡ የስራ ውል መቋረጡን ተከትሎ 1ኛ አመልካች የዋስትናውን ገንዘብ ገቢ እንዲያደርግ ተጠሪ ቢጠይቀውም የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ የዋስትና ግዴታውን ለመወጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ 1ኛ አመልካች በመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና መሰረት ብር 45‚844‚565 ክፍያ እንዲፈጽም ከተጠየቀበት ግዜ ከ27/6/2010ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፍል እንዲወሰንበት በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ… Previous Article አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594 Next Article አቶ ጉዕሽ ካሳ ደሞዝ እና እነ አቶ አማኑኤል ወልደሊባኖስ ተስፋዬ የሠ/መ/ቁጥር 243564 Print 6131 Documents to download 246233(.pdf, 1.05 MB) - 744 download(s)
BRICS Chief Justices' Forum Concludes BRICS Chief Justices' Forum Concludes Sunday, September 6, 2026 16 September 6, 2026 (Federal Supreme Court) The BRICS Chief Justices forum, hosted by the Supreme Court of India from September 4 to September 6, 2026, has concluded. Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ... Monday, August 31, 2026 52 ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሠራተኞችን መብት፣ ግዴታና የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮችን በማካሄድ ተጠናቋል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመታዊ የሰራተኞች መድረክ... Monday, August 31, 2026 52 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሰራተኞች መድረክ በዛሬው ዕለት መካሄድ የጀመረ ሲሆን የፍርድ ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዷል። Read more
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በቀጣይ የአምስት... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በቀጣይ የአምስት... Friday, August 28, 2026 76 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክቡራን ዳኞች የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን የቀጣይ አምስት ዓመታት (2019-2023) የስትራቴጂክ ዕቅድ ረቂቅ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሂደዋል። Read more