አቶ ሰይድ እንድሪስ እና የሸዋ ሮቢት...

ጉዳዩ የውርስ ሀብት ነዉ የተባለዉን የመሬት ይዞታ አስለቅቆ ለመረከብ በቀረበ ክስ መነሻ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ተብሎ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ አመልካቾች በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ሮቢት ከተማ... Read more

ኦዲት ሰርቪስ ኮርፖሬሽን እና ፀጋ ረታ...

አመልካች የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባቀረበው ክስ አመልካች የኮምፒዩተር እቃዎችን ለመግዛት ባወጣው ጨረታ ተጠሪ አሸንፎ እቃዎቹን አቅርቦ ክፍያ የተቀበለ ቢሆንም እቃዎቹን ከሰርቨሩ ጋር የሚያገናኙ ኬብሎችን ባለማቅረቡ ምክንያት... Read more

የሟች ወ/ሮ ዋጋዬ ወ/ማርያም እና ወ/ሮ...

መዝገቡ ከቀነ ቀጠሮ በፊት ሊቀርብ የቻለው አመልካች 15/4/ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ ቃለ መሃላ ስላቀረቡ ነው፡፡ ለዚህ ችሎት 7/4/2014 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ  ችሎት በመ/ቁ 279892... Read more

እነ ሲሳይ ጥላሁን እና ወሰኔ ጥላሁን...

መዝገቡ ከቀነ ቀጠሮ በፊት ሊቀርብ የቻለው አመለካች 01/04/2014 ዓ.ም በተፃፈ ቃለ መሃላ አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡  ለዚህ ችሎት 28/03/ቀን 2014 ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ ፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት... Read more
1345678910Last
«January 2022»
MonTueWedThuFriSatSun
272829303112
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31123456

ዳኞች የዕግድ አሰጣጥና አፈጻጸምን በሚመለከቱ ሕጎች ላይ...

52

ዳኞች ከአገር ኢንቨስትመንት፣ ከሕዝብ ጥቅም እንዲሁም ከግለሰብ ክርክሮች ጋር በተያያዘ   በዕግድ አሰጣጥና አፈጻጸም ዙሪያ የሚወስኑትን ጉዳይ ማየትና መፈተሽ እንዲሁም በሕጎች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በየጊዜው ሊያዳብሩ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

ይህ የተገለጸው ከሶስቱ ፌደራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ ዳኞች ከዕግድ አሰጣጥና አፈጻጸም ጋር በተያያዘ በፌደራል ፍርድ ቤቶች የተዘጋጀውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የፌዴራል ፍርድ ቤት መር አስማሚነት...

1146

የፍርድ ቤት መር አስማሚነትን የሚያግዝ የአስማሚዎችን የዲሲፕሊን ጉዳዮች የሚመረምር ኮሚቴ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 45(7) መሰረት መቋቋም ስለሚያስፈልገው እና የኮሚቴውንም ዝርዝር ሃላፊነት፤ አወቃቀር እና የተጠያቂነት ወሰን መደንገግ ስለሚያስፈልግ፤

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 45(8) እና 48(4) በተሰጠው ስልጣን መሰረት የፍርድ ቤት መር የአስማሚነት መመሪያ ወጥቷል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያወጣው መመሪያ የፌዴራል ፍርድ ቤት መር አስማሚነት መመሪያ ቁጥር 12/2014 በሚል ስያሜ ይጠራል፡፡ 

ባለፉት ሶስት ዓመታት በተከናወኑ የማሻሻያ ስራዎች ተስፋ...

92

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች እየተከናወኑ ባሉ የማሻሻያ ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መገኘታቸውን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞችና የአስተዳደር ዘርፍ ሃላፊዎች እንዲሁም የስር ፍርድ ቤቶች ፕዝደንቶችና ም/ፕሬዝደንቶች በተገኙበት በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ገለጹ፡፡

የውይይት መድረኩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከጀስቲስ ፎር ኦል- ፐሪዝን ፌሎው ሺፕ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሂደት የፍርድ ቤቶች ሚናን አስመልክቶ ዳኞች በሙያቸው ያገኙትን ዕውቀትና እና አመለካከት እርስ በእርስ እንዲለዋወጡ ማስቻል እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማሻሻያ ስራዎች ያስገኙትን ውጤት መገምገም ዓላማ ያደረገ ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ በስትራቴጂያዊ እና ዓመታዊ ዕቅዱ ላይ ለምክር...

59

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ፍትህና የዲሞክራሲ ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ፍርድ ቤቱ ባዘጋጀው ሶስተኛው ስትራቴጂያዊ ዕቅድ እና ዓመታዊ ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ሰጠ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በፍርድ ቤቱ በኩል ዕቅዶቹን አስመልክቶ ሰፊ ማብራሪያ ከመቅረቡ በፊት በሰጡት አጭር ገለጻ የዳኝነት ዘርፉ በአማካሪ ድርጅት በመታገዝ ስትራቴጂያዊ ዕቅዱን ማዘጋጀቱን፤ የዕቅዱን ይዘትና አዘገጃጀት ሂደት የሚከታተል በየደረጃ ያሉ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች አባል የሆኑባቸው ዓቢይና ቴክኒክ ኮሚቴ መቋቋማቸውን፤ በረቂቅ ዕቅዱ ላይ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማህበረሰብ እና ባለድርሻ አካላት መወያየታቸውን እና የተገኙ ተጨማሪ ግብዓቶችን በማካተት ተዘጋጅቶ የጸደቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

245678910Last