አብይ ሻንቆ እና እነ ወ/ሮ ጥሩነሽ...

የጉዳዩ መነሻ የሆነዉ የአሁኑ አመልካች 2ኛ ተከሳሽ በመሆን የአሁን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ ሲሆኑ የአሁን 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን በነበረዉ በንግድ ድርጅት ዉስጥ ያሉትን የንብረቶች ግምትና የታጣ ጥቅም ከሳሽ... Read more

አቶ ጋዲሳ ተሾመ ቤኛ ፤ ወ/ሮ ወርቅነሽ...

ጉዳዩ የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ የመቃወም አመልካች፤ የአሁን አመልካቾች ደግሞ የመቃወም... Read more

ወ/ሮ ሽብሬ ልዑል ሰገድ የሕጻን ኤልሻዳይ...

ጉዳዩ ኑዛዜ እንዲፈርስ በሚል የቀረበን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች አመልካች፤ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተጠሪ በመሆን... Read more

ዶ/ር ቻላቸው ሲሳይ እና ወ/ሮ ቅድስት...

ጉዳዩ የባልና ሚስት ንብረት ክርክርን የሚመለከት ሆኖ አቤቱታው በቀረበበት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ አመልካች የሰበር አመልካች ደግሞ በተጠሪነት ተከራክረዋል፡፡ የፍቺ ውሳኔን ተክትሎ ተጠሪ ሐምሌ 28 ቀን 2013... Read more
12345678910Last
«July 2024»
MonTueWedThuFriSatSun
24252627282930
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
2930311234

ፍርድ ቤቱ ሐሰተኛ የቃለ-መሐላ አቤቱታ ያቀረቡ ባለጉዳይን...

632

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ሰበር ችሎት ሐሰተኛ ቃለ-መሐላ አቤቱታ ያቀረቡ ባለጉዳይን በችሎት መድፈር ጥፋተኛ ናቸው በማለት ሐምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ቀላል እስራት እንዲቀጡ ወሰነ፡

ፍርድ ቤቱ በእስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው አቶ ኃይለማርያም ወዳጆ በደሀ ደንብ መስቀልኛ የሰበር አቤቱታ ለማቅረብ የዳኝነት ለመክፈል ምንም ሀብት እና ንብረት የሌላቸውና በቀበሌ ቤት የሚኖሩ መሆኑን በቃለ-መሐላ በማረጋገጥ አቤቱታቸውን በሀሰተኛ መንገድ በማቅረባቸው ነው፡፡

ዜና መግለጫ

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1-30 ባለው ጊዜ መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት መስጠታቸውን ይቀጥላሉ

689

በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀፅ 38(2) መሰረት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ባለው ጊዜ ዝግ እንደሚሆኑ ይደነግጋል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ዳኞች ባላቸው የትርፍ ጊዜ አስቸኳይ የሆኑ ጉዳዮችን ብቻ ሊያስተናግዱ እንደሚገባም አዋጁ ያስቀምጣል፡፡ ዳኞች ዓመቱን ሙሉ እጅግ አድካሚ የሆነ የዳኝነት አግልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ በዚህም አዎንታዊ የሆኑ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡ ይህን ስራ ይበልጥ ለማስቀጠል፣ ወደ 2015 ዓ.ም የሚያልፉ መዝገቦችን ቁጥር ለመቀነስ፣ የበሰሉ መዝገቦችን እልባት ለመስጠት፣ እስረኛ ያለባቸውን መዝገቦች ቅድሚያ ሰጥቶ ለመስራት እንዲያስችል በዳኞች ፈቃደኝነት ላይ በመመስረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶቹ ከነሐሴ 1-30/2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ መደበኛውን የዳኝነት አገልግሎት መስጠታቸውን የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡

«ትልቁ የመሪዎች መለያ አውቃለሁ ባይነት ሳይሆን ለመማር...

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክብርት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ

580

ክብርት ፕሬዚደንትዋ ይህን የገለጹት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንትና የፌደራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ የሆኑት ክቡር አቶ ተስፋዬ ንዋይ «የአመራር ክህሎት» በሚል ርዕስ ያሳተሙትን መጽሐፍ ሐምሌ 2 ቀን 2014 ዓ.ም በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል ለማስመረቅና ለማስገምገም በተዘጋጀ ሥነሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ሆነ የዳኞች አስተዳደር...

623

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በአዋጅ ቁጥር 1233/2013 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ለመተግበር ያስችለው ዘንድ የተከማቹ መዛግብትን በቅድሚያ ማጥራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጾ ጊዜያዊ ዳኞች እንዲመደቡለት ያቀረበውን ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ይህንን ተከትሎ ጉባዔው በፌዴራል ዳኝት አስተዳደር አዋጅ  ቁጥር 1233/2013 አንቀጽ 26 (2) ከአንድ ፍርድ ቤት ወደ ሌላ የፍርድ ቤት ደረጃ በጊዜያዊነት ዳኞችን መድቦ የማሰራት ስልጣኑን ተጠቅሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሸክምን ይወጣሉ ያላቸውን አራት የከፍተኛ ፍርድ  ቤት ዳኞች ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ የመዝገብ ክምችት እንዲያጠሩ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ 

First2526272830323334Last