በሪፖርቱ በእቅድ ዝግጅት ምዕራፍ ላይ የተከናወኑ ተግባራት፣ የዳኝነት ነጻነትና ተጠያቂነት መርሆዎችን ከማጠናከር፣ ቅልጥፍናና ጥራትን ከማሳደግ ፣የፍ/ቤቶችን ተደራሽነት ከማስፋፋት፣ አገራዊና አለምአቀፋዊ አጋርነትን እንዲሁም የመምራትና የመፈጸም ብቃት ከማሳደግ አኳያ የተከናወኑ ተግባራት የተዘረዘሩ ሲሆን በተጨማሪነትም የኢኮቴ አጠቃቀም እና የፋይናንስና ንብረት ውጤታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት በሰፊው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡