የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽሕፈት ቤት ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አለም አቀፍ ናርኮቲክ እና ሕግ ማስከበር ቢሮ (Department of State’s Bureau of International Narcotics and Law Enforcement (INL)) ከመጡ ልኡካን ጋር ሐሙስ መጋቢት 19/2016 የጽሕፈት ቤቱን አቅም በዘላቂነት መገንባት በሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አካሂዷል።