በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጽህፈት ቤት የከፍተኛ ኮሚሽነር -ምስራቅ አፍሪካ ክልላዊ ጽህፈት ቤት (OHCHR-EARO) ከኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ምክክር መድረክ ፕሮፌሰር ክሪስቶፈር ሚባዚራ የህዝብ ጥቅም ሙግት ከኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና የባህል መብቶች አንጻር ያለውን አንድምታ ሰፊ ማብራሪያ ያቀረቡበትና ውይይት የተደረገበት ሲሆን ታከለ ቡልቶ (ዶ/ር) በበኩላቸው አለምአቀፍ የሰብአዊ መብቶችና እነዚህን መብቶች ለማስፈጸም የሀገር ውስጥ ህጎችን ሚና በተመለከተ ትንትና አቅርበዋል፡፡