የሰበር ውሳኔዎች

 

ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ...

የአሁን አመልካች በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ/መ/ቁ 47863 እና በመ/ቁ በመ/ቁ 47862 በሁለቱም መዝገቦች ላይ 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው የክስ ይዘትም አመልካች የኢትዮጵያ የፌዴራል ቡና... Read more

አቶ መሀመድ አለሙ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ...

ጉዳዩ የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ አሁን የክርክሩ አካል ያልሆነው የትኦትኦ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ 2ኛ ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ በስር ፍርድ... Read more

ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና...

የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ለአመልካች በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/2 በ4/11/2015ዓ.ም በተጻፈ በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/1 በ9/10/2015 በተጻፈ የምደባ ደብዳቤ ላይ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ውስጥ በደረጃ XVIII በመደብ... Read more

አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ...

ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ... Read more
12345678910Last
«July 2025»
MonTueWedThuFriSatSun
30123456
78910111213
14151617181920
21222324252627
28293031123
45678910

የዳኝነት ስርዓቱን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ፍርድ ቤቱ...

1022

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓቱን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት በቅርቡ ከተቋቋመው የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ገለጹ፡፡

ክቡር አቶ ሰለሞን ይህን የገለጹት በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው በአዲሱ የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ መሰረት ለተቋቋመው የጠበቆች ማህበር ስራ ማስጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በእንግድነት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡

ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ በሰጡት የማጠቃለያ አስተያየት...

913

ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ (የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት) ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም «ፍርድ ቤቶች እና የሽግግር ፍትሕ፤ ግጭቶች ሲከሰቱ ወይም ከግት በኋላ» በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ሲምፖዚየም ላይ ከተሳታፊዎች የቀረቡ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ በሰጡት የማጠቃለያ አስተያየት ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ዋና ዋናዎቹ፡-

• ሲምፖዚየሙን ማዘጋጀት ያስፈለገው አሁን አገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ የዳኝነት ተቋሙ ሊኖረው ከሚችለው የዳኝነት ሚና ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

በፌዴራል ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት 204 ፋይሎች ታይተው...

1094

በፌዴራል ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት 204 ፋይሎች ታይተው 68 ፋይሎች እልባት ማግኘታቸው ተገለጸ

በተለያየ የሃራችን ክፍሎች የተፈጠሩ ግጭቶች ጋር በተገናኘ በፌዴራል ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት 204 ፋይሎች ታይተው 68 ፋይሎች እልባት አግኝተዋል፡፡

በእያንዳንዱ ፋይል የተከሳሾች ቁጥር በአማካይ ከ 50 – 200 እንደሚድረስ የገለጹት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ ጉዳዩቹ ደግሞ እጅግ ውስብስብ ናቸው ብለዋል፡፡

ክብርት ፕሬዚደንትዋ «ፍርድ ቤቶች እና የሽግግር ፍትሕ፤ ግጭቶች ሲከሰቱ ወይም ከግጭት በኋላ » በሚል ርዕስ በስካይ ላይት ሆቴል ጥር 9 ቀን 2014 ዓ.ም በተዘጋጀ ሲምፖዚየም መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በሀገራችን በተከሰቱ ግጭቶች ሕግንና ሞራልን የጣሱ በርካታ ተግባሮች እንደተከናወኑ ገልጸው በሴቶች እና ሕጻናት ላይ የተፈጸመው ወንጀል ደግሞ ሊታለፉ ከማይገባቸው ወንጀሎች የሚመደብ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ክስ የተቋረጠባቸው ሶስት የክስ መዝገቦች የስነ-ስርዓት...

1443

ባለፈው ሶስት ዓመት ተኩል የፌደራል ፍ/ቤቶች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በተገቢው ደረጃ ለማከናወን በርካታ የለውጥ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የለውጥ እርምጃዎች ትኩረት ያደረጉት በተቋማዊ እና በግለሰብ ዳኞች ደረጃ የፍ/ቤቱን ነጻነት እና ገለልተኝነት ማስከበር ነው፡፡ በተጓዳኝም ለተጠያቂነት ተቋማዊ ስርዓቶች ተዘርግተዋል፡፡ በፍ/ቤቱ አመራሮች እና ዳኞች በኩል ሲደረግ የነበረው ጥረት ዋናው ግብ የሚሰጠው የዳኝነት ዘርፍ ቀልጣፋ፣ ተገማች እና ተደራሽ በማድረግ በፍ/ቤቱ አገልግሎት ላይ የሕዝብ አመኔታ እንዲጨምር ነው፡፡

በዚህ ወር መጨረሻ በሚዘጋጀው “የፍ/ቤቱ አሁናዊ ሁኔታ” ጉባዔ እንደሚገልጸው በተለያየ ደረጃ የፍ/ቤቱ አገልግሎትም ሆነ ተደራሽነት እያደገ የመጣ ለመሆኑ ፍ/ቤቱ በገለልተኛ የጥናት ተቋም የሰራው የሕዝብ አስተያየት ሰርቬይ  “public perception survey” አመልክቷል፡፡

First4748495052545556Last