በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲረዳ በተለያየ መደብና ስራ ክፍሎች ሲከናወን የነበረውን የሬጅስትራር አገልግሎት ወደ አንድ ማዕከል ሰብሰብ በማድረግ ባለሙያዎች እና ሰራተኞች በቡድን እና በትብብር መርህ ስራቸውን እያከናውኑ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡
ይህን የገለጹት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ቦጃ ታደሰ በፍ/ቤቱ የሬጅስትራር አገልግሎትን ለሚያከናውኑ ባለሙያዎች እና ሰራተኞች በጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ ላይ ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም በፍ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሲሰጡ ነው፡፡