2794
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኝነት አገልግሎት ዘርፍ እና በአስተዳደር ሥራዎች ዘርፍ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎችን ሊሸከም የሚችልና የሥነምግባር መርሆዎችን በአግባቡ የተገነዘበ፣ በሥነምግባር እሴቶች እየተመራ ኃላፊነቱን እና ሥራውን በአግባቡ ሊያከናውን የሚችል የፍርድ ቤት ማሕበረሰብ መገንባት አስፈላጊ መሆኑን በፍርድ ቤቱ የክቡር ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቦጃ ታደሰ ገለጹ፡፡
ለፍርድ ቤቱ የአስተዳደር ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች በሥነምግባር፣ በሙስና እንዲሁም ተያያዥ በሆኑ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ የተዘጋጀ የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በፍርድ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ተሰጥቷል፡፡
3990
ለፍርድ ቤቱ አዲስ ሠራተኞች የሙያ ትውውቅ ኮርስ (Induction Training) ተሰጠ
--------------------------------------------------------------------------
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥነምግባር መከታተያ ክፍል “ሙስናና ብልሹ አሠራርን መከላከልና መልካም ሥነምግባርን ማስፈን” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሥልጠና ከፍርድ ቤቱ የአስተዳደር ዘርፍ ለተውጣጡ 120 ሠራተኞች ሚያዚያ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በፍርድ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ተሰጠ፡፡
2954
በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በፌደራል ፍርድ ቤቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ ለተለዩ የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥራዎች ማስፈጸሚያ የአውሮፓ ሕብረት የመደበው የገንዘብ ድጋፍ ውጤታማ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል የፍርድ ቤቱ አመራሮችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ተገቢውን ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ ገለጹ፡፡
2545
የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በአራት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ሶስት ጉዳዮች ላይ ለውሳኔ አሰጣጥ እንዲያመች ተጠሪዎች መልስ እንዲሰጡበት አቅጣጫ ሲያስቀምጥ በአንድ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ተጣርተው እንዲቀርቡ ትእዛዝ በማስተላለፍ በይደር አሳልፎታል፡፡