የሰበር ውሳኔዎች

 

ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት...

በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ አስተዳደራዊ ተግባርን ለማከናወን በተሰማሩ ሰራተኞች የሚነሱ  የስራ ክርክሮችን በተመለከተ ፍርድ ቤቶች የስራ ክርክሩን ተቀብለው አከራክረው ለመወሰን ህጋዊ የዳኝነት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ ትርጉም... Read more

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት...

ከ2002 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎችን ያጠቃለለ መጽሐፍ በልዮ ዕትም ለንባብ ምቹ ሆኖ ቀርቧል። Read more

ወ/ሮ የማርውሃ ወርቅነህ እና እነ ወ/ሮ...

የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ከሳሽ አመልካች ደግሞ ጣልቃ ገብ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪዎች በቀን 11/09/2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ የእናታቸው ወ/ሮ ሸዋነሽ ስመኝ... Read more

ጨመሬ ቶሎሳ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ...

የአሁን አመልካች በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ/መ/ቁ 47863 እና በመ/ቁ በመ/ቁ 47862 በሁለቱም መዝገቦች ላይ 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው የክስ ይዘትም አመልካች የኢትዮጵያ የፌዴራል ቡና... Read more
12345678910Last
«January 2026»
MonTueWedThuFriSatSun
2930311234
567891011
12131415161718
19202122232425
2627282930311
2345678

የፍርድ ቤቱ ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀንን አከበሩ

1752

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ23ኛ ጊዜ በመከበር ላይ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሀገራችን ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ “በትዉልድ ቅብብሎሽ ኢትዮጵያ ትፀናለች” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን ቀኑ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠራተኞች ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ/ም በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡

በዓሉ በፍርድ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ሲከበር የፍርድ ቤቱ ሴቶችና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ወርቅነሽ በቀለ ባደረጉት የመክፈቻ ላይ ንግግር እንደገለጹት ከሰባት ቢሊዮን በላይ ከሚገመተዉ የዓለም ህዝብ መካከል የወጣቱ ቁጥር 1.8 ቢሊዮን እንደሚደርስና ከዚህ ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆነዉ ወጣት በማደግ ላይ በሚገኙ ሀገራት እንደሚገኝ ጠቅሰው ከሀገራችን የህዝብ ብዛትም 31.8 በመቶ ያህሉ ከፍተኛ አቅም ያለዉ አምራች ኃይል የሆነዉ የወጣቱ ክፍል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዳኞች በማያቋርጥ ሒደት ብቃታቸውን ሊያሳድጉና በሥልጠና...

1643

ዳኞች በማያቋርጥ ሒደት ብቃታቸውን ሊያሳድጉና በሥልጠና ሊያልፉ እንደሚገባ ተጠቆመ።

ዳኞች በማያቋርጥ ሒደት ብቃታቸውን ሊያሳድጉና በሥልጠና ሊያልፉ እንደሚገባ ይህም የዳኝነት ነጻነትን ለማስጠበቅና ክህሎታቸውን ለማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ም/ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ተþሊት ይመስል ገለጹ፡፡

ከፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ ከፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ከፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተውጣጡ 350 ያህል የፌደራል ፍ/ቤቶች ዳኞች የተሳተፉበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ከነሐሴ 21-22 ቀን 2014 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ተካሒዷል፡፡

የፍርድ ቤቱ ዳኞች እና የአስተዳደር ዘርፍ የሥራ ክፍሎች...

1660

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች እና የአስተዳደር ዘርፍ የሥራ ክፍሎች በ2014 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምና በ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከነሐሴ 4-7 ቀን 2014 ዓ.ም ግምገማ አካሄዱ፡፡

የፍርድ ቤቱ ዳኞች ነሐሴ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ያካሔዱት የአንድ ቀን የሥራ አፈጻጸም እና የዕቅድ ግምገማ የተመራው በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት በክብርት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ሲሆን በመድረኩ ላይ የችሎቶች ዕቅድ አዘገጃጀትን የተመለከተ ማብራሪያም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ፍርድ ቤቱ ሐሰተኛ የቃለ-መሐላ አቤቱታ ያቀረቡ ባለጉዳይን...

1710

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ሰበር ችሎት ሐሰተኛ ቃለ-መሐላ አቤቱታ ያቀረቡ ባለጉዳይን በችሎት መድፈር ጥፋተኛ ናቸው በማለት ሐምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ቀላል እስራት እንዲቀጡ ወሰነ፡

ፍርድ ቤቱ በእስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው አቶ ኃይለማርያም ወዳጆ በደሀ ደንብ መስቀልኛ የሰበር አቤቱታ ለማቅረብ የዳኝነት ለመክፈል ምንም ሀብት እና ንብረት የሌላቸውና በቀበሌ ቤት የሚኖሩ መሆኑን በቃለ-መሐላ በማረጋገጥ አቤቱታቸውን በሀሰተኛ መንገድ በማቅረባቸው ነው፡፡

First5657585961636465Last