የፌደራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 እና ሌሎች ተከታታይ የአዋጁ ማሻሻያዎችን በመሻር በጥር ወር 2013 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጸደቀው አዲስ አዋጅ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍትሐ ብሔር ስረ-ነገር ሥልጣን ላይ ለውጥ ማድረጉን ተከትሎ በፌዴራል መጀመሪያ ድረጃ ፍርድ ቤት ሊኖር ስለሚችል የችሎት አደረጃጀት እና የዳኞች አሰያየምን ለማመላከት የተካሄደ የዳሰሳ ጥናት ውጤት ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ለፍ/ቤቱ አስተባባሪ ዳኞች፤ ዳኞች፣ ለሬጂስትራሮችና ለልዩ ልዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች ለአስተያየት ቀረበ፡፡