የአቶ ቃሲም እድሪስ እና አቶ አብዱርሃማን...

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የከተማ ይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም የአሁን ተጠሪ በአመልካች እና በሌላ አንድ ግለሰብ ላይ በሲናና ወረዳ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ጭብጥም ቦታና አዋሳኙ... Read more

እሸቱ ይመር እና መብራቱ ታደሰ...

ጉዳዩ የይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን... Read more

ሳንቴ የህክምና ማዕከል እና ወ/ሮ ህይወት...

ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረውም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ በአመልካች ላይ በቀን... Read more

እነ ዳዊት መንገሻ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ...

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የእምነት ማጉደል ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩም የተጀመረው የአሁን ተጠሪ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 675(1) ድንጋጌን ጠቅሶ በአሁን አመልካቾች ላይ በባሌ ዞን ጋሰራ ወረዳ ፍርድ... Read more
First376377378379381383384385Last
«September 2023»
MonTueWedThuFriSatSun
28293031123
45678910
11121314151617
18192021222324
2526272829301
2345678

በሽግግር ፍትሕ ሂደት የዳኞች ሚና በሚል ርዕስ ሀገራዊ...

66

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢጋድ ጋር በመሆን ለሶስት ቀናት በሽግግር ፍትሕ የዳኞች ሚና በሚል ርዕስ በቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ወርክሾፕ ተጠናቀቀ፡፡

ወርክሾፑን በንግግር የከፈቱት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ እንደገለጹት ዳኞች አድካሚ የዳኝነት ስራ አጠናቀው በሚገኙበት በአሁኑ የእረፍት ጊዜ የዳኞችን አቅም ለማገንባት የሚያስችል፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት በተሰጠው የሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ ወርክሾፕ መዘጋጀቱ በቀጣይ የሚቀርቡ የሽግግር ፍትሕ ጉዳዮች ላይ በቂ ግንዛቤ እና እወቀት በመያዝ ለመስራት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት...

132

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አዲስ ለሚያሰራው የህጻናት ማቆያ የሚሆን ግምታቸው ብር 35,000 (ሰላሳ አምስት ሺህ) ብር የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

ዜና መግለጫ

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2016 ዓ.ም ድረስ በከፊል ዝግ ይሆናሉ፡፡

107

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ እና በሕግ በተሰጣቸው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት የሚቀርቡ ጉዳዮችን በማስተናገድ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲጠበቁ ሰላም እና ስርዓት እንዲከበር የማድረግ ተግባራትን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

በዚህ መሰረት በ2015 በጀት ዓመት በነበረዉ የመዛግብት አፈጻጻም አንጻር ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች በአጠቃላይ 213,116 መዛግብት ቀርበዋል። ከእነዚህም ዉስጥ ለ184,467 (86.56%) መዛግብት እልባት መስጠት የተቻለ ሲሆን 28,675 (13.44%) መዛግብት ደግሞ ወደ 2016 በጀት ዓመት ተሻግረዋል፡፡ የበጀት ዓመቱ አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2014 በጀት ዓመት ለፌ/ፍ/ቤቶች የቀረቡት 209,317 መዛግብት ሲሆኑ ዕልባት ያገኙት ደግሞ 176,767 ነበሩ፡፡ በዚህም መሠረት በ2015 በጀት ዓመት የቀረቡት መዛግብት በ2014 በጀት ዓመት ከቀረቡት በ3,799 (1.8%) ከፍ ያሉ ሲሆን በተመሳሳይ ዕልባት ያገኙትም በ7,670 (4.3%) መዛግብት ከፍ ያሉ ናቸው፡፡

የፍርድ ቤቶቹ አፈጻጸም በተናጠል ሲታይ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት 26,185 መዛግብት ቀርበው ለ19,201 ዕልባት የተሰጠ ሲሆን 6,984 መዛግብት ወደ 2016 በጀት ዓመት ተሻግረዋል፡፡ በተመሳሳይ በ2015 በጀት ዓመት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት የመዛግብት ብዛት 33,721 ሲሆን 26,301 መዛግብት ዕልባት አግኝተዋል፡፡ ወደ 2016 የተሻገሩት መዛግብት ብዛትም 7,420 ሆኗል፡፡ እንዲሁም ለፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት የቀረቡት 153,210 መዛግብት ሲሆኑ 138,965 ዕልባት በማግኘታቸው 14,245 ወደ 2016 በጀት ዓመት ተላልፈዋል፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ...

164

(ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም፣) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክቡራን ፕሬዚዳንቶች ፣ ክቡራን ዳኞች እና የሥራ ኃላፊዎች የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐግብር በአዲስ አበባ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ተከናወነ፡፡

12345678910Last