በቀን 02/02/17 ዓ.ም በጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በተለያዩ ርዕሶች ማለትም የፍ/ቤት ዲጂታላይዜሽን ስራዎች፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች ላይ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም፣ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(INSA)፣ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ተቋማት በተገኙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቋል፡፡