“ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች አተገባበር በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች” በሚል ርዕስ ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና የህግ ባለሙያዎች የአንድ ቀን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ የህዝብ ጥቅም የሚነኩ ክርክሮች ጽንሰ ሃሳባዊ ማዕቀፎችን፣ በኢትዮጵያ ሃገራዊ የዳኝነት ስልጣን ወሰን የሰብዓዊ መብቶችን የተመለከቱ ክርክሮችን ለመዳኘት የሚያግዙ በስራ ላይ ያሉ የህግ ማዕቀፎች እንዲሁም መሰረታዊ መብቶችንና ነጻነቶችን ለመተግበር የሚረዱ የህግ ማዕቀፎችን በስልጠናው ለተሳተፉ ዳኞችና ህግ ባለሙያዎች ማስገንዘብ እና የጋራ መረዳት መፍጠር ነው፡፡