የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አደረገ

23

በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡ የሚስተዋሉ ክፍተቶችና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም መፍትሄዎች ማስቀመጥ የሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ የሚመክር የዉይይት መድረክ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

የፌደራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት አዋጅ ማሻሻያ እና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ

30

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የፌደራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በጋራ በመሆን የፌዴራል የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 188/92 እንዲሻሻል የጥናት ሰነድ እና የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ አዘጋጅ ቡድን ላደረጉት የስራ ትጋትና አስተዋጽኦ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም የምስጋና መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

በወንጀል ነክ ድርጊት ዉስጥ ገብተዉ ከተገኙ ህጻናት እንዲሁም በሴቶች እና ህጻናት ችሎት ለሚሰሩ የፌዴራል ዳኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

67

በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በወንጀል ነክ ድርጊት ዉስጥ ገብተዉ ከተገኙ ህጻናት እንዲሁም በሴቶች እና ህጻናት ችሎት ለሚሰሩ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰኔ 14 እና 15 ቀን 2017 ዓ.ም ተሰጥቷል፡፡

የኢ-ፋይሊንግ እና የፕላዝማ ችሎት የስራ ማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሄደ

137

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጋር በመተባበር በገላን ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት ማዕከል ያሰራውን የኢ-ፋይሊንግ እና የፕላዝማ ችሎት ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ስራ አስጀምሯል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

138

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የሁለቱን ተቋማት የትብብር መስክ ያጠናክራል የተባለ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ልዑካን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ

149

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ልዑካን ሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ከኡጋንዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት (ቺፍ ጀስቲስ) ክቡር ሚ/ር አልፎንሴ ኦዊኒ ዶሎ ጋር ተወያዩ፡፡

116

በውይይታቸውም አፍሪካ ተኮር የሆኑ አማራጭ የሙግት መፍቻ ዘዴዎችን በውጤታማነት ለመተግበር ፍርድ ቤቶች ያላቸውን ወሳኝ ሚና እና በአህጉር ደረጃ በተቋቋመው የአፍሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንቶች አማራጭ የሙግት መፍቻ መድረክ (African Chief Justices ADR Forum) ኢትዮጵያ በአባልነት መሳተፍ በምትችልበት ሁኔታ እንዲሁም በሌሎች የዳኝነት ስርዓት ማሻሻያ ስራዎች ዙሪያ መክረዋል፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ዘዴ አቤቱታ አቀራረብ፣ ሙግት ማከናወን እና የሪከርድ አሰራር እና አስተዳደር መመሪያ ረቂቅ ላይ ከፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተደረገ

288

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ዘዴ አቤቱታ አቀራረብ፣ ሙግት ማከናወን እና የሪከርድ አሰራር እና አስተዳደር መመሪያ ረቂቅ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ የፌደራል መጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ዳኞች፣ ሬጅስትራሮች እንዲሁም ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ በቀን 22/09/2017 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

1345678910Last