ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች መድረክ ተካሂዷል
/ Categories: News

ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች መድረክ ተካሂዷል

ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች መድረክ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት እንዲሁም የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩም የፍርድ ቤቶቹን የለውጥ ፍኖተ ካርታን መሰረት አድርጎ የተነሱ መልካም ተሞክሮዎች ላይ ሀሳብ አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡

በውይይቱም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአጭር ግዜ እያመጣ ያለው ለውጥ፣ የፍርድ ቤትን ችግር ከህዝብ ጋር የመፍታት ሁኔታ ከሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲሁም ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት ከኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የውስጥ ገቢ አጠቃቀምና የስርዓት ግንባታ ከሐረሪ ክልል ፍርድ ቤት እንደ መልካም ተሞክሮ ከተነሱት ጥቂቶቹ ናቸው።

በሌላ በኩል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተመለከተ ሁሉም የፍትህ አካላት ከፍርድ ቤቶች እኩል ካልሄዱ ፍርድ ቤቶች ብቻቸውን ሊያሳኩት የሚችሉት ለውጥ የማይመጣ በመሆኑ ባለድርሻ የፍትህ አካላት ከፍርድ ቤቶች ጋር እኩል መራመድ እንዳለባቸው ተነስቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የፍርድ ቤቶችን አሰራር ማዘመን እና የጋራ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ በቅንጅት መስራት የጋራ ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግ ህብረተሰቡም በፍርድ ቤቶች ላይ ያለው አመኔታ እንዲጨመር ባለው አቅም መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

አክለውም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስኬት ባለው መጠቀምን መሰረት ያደረገ በመሆኑ እንደ ጥሩ ምሳሌ መነሳት የሚችል መሆኑን ጠቅሰው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአጭር ግዜ እያመጣ ያለውን ለውጥ አድንቀዋል። በጣም የተጎዱ አካባቢዎች ላይ ያሉ ፍርድ ቤቶችን ለመደገፍ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመው ሌሎች የጋራ አጀንዳዎች ላይም በሰፊው የጋራ ውይይቶች እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

Previous Article ሀገር አቀፍ የዳኝነትና የፍትህ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ
Next Article ዓለም አቀፍ የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከበረ
Print
1034