Monday, June 2, 2025 / Categories: News ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሴት ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የአመራርነት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሴት ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች "ሴቶችና አመራርነት" በሚል ርዕስ በቀን 22/09/2017 ዓ.ም የአመራርነት ክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናውን የሰጡት የተከበሩ ዶክተር ከበደ ገነቲ ሲሆኑ በስልጠናው ስለ አመራርነት ህጎችና መርሆዎች፣ ሴቶች በአመራርነት ውስጥ ያላቸው ሚና፣ ሴቶች ወደ አመራርነት እንዳይመጡ የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች እንዲሁም መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ሰፊ ገለጻና ዉይይት ተደርጓል። Previous Article የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኞች የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ Next Article የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ዘዴ አቤቱታ አቀራረብ፣ ሙግት ማከናወን እና የሪከርድ አሰራር እና አስተዳደር መመሪያ ረቂቅ ላይ ከፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተደረገ Print 812