Monday, December 1, 2025 / Categories: News ለፌደራል ፍርድ ቤቶች የቤተሰብ ችሎት ዳኞች የልምድ ልውውጥ መርሃግብር ተካሄደ የኢንግላንድ እና ዌልስ ጠበቆች ማህበር ፕሬዚዳንት የሆኑት ክብርት ባርባራ ሚልስ በቀን 19/03/2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ለፌደራል ፍርደ ቤቶች የቤተሰብ ችሎት ዳኞች ልምዳቸውን አካፈሉ፡፡ ፕሬዝዳንቷ ቤተሰብ የአገር መሠረት እንደመሆኑ መጠን የቤተሰብ ነክ ጉዳዮች እንደሌሎች የፍትህ ዘርፎች የዳኝነት አካላትን እና የህጉ ማህበረሰብ ልዩ ትኩረት የሚሹ መሆኑን በማንሳት ላለፉት 35 ዓመታት በቤተሰብ ጉዳዮች ዙሪያ በማሰልጠን፤ በዳኝነት፤ በህግ ማማከር እና በማስማማት ያካበቱትን ልምድ መነሻ በማድረግ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡ ከልምድ ለውውጡ ባሻገር ፕሬዚዳንቷ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተጀመሩ የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይት እና ጉብኝት አድርገዋል፡፡ Previous Article የላይቤሪያ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትና ልዑክ ቡድናቸው በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ Next Article የአፍሪካ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቶችና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንቶች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ Print 483