ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባል የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ
/ Categories: News

ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባል የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ

ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባል ለነበሩት ፕሮፌሰር ሙራዱ አብዶ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 09/04/2018 ዓ.ም የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

ፕሮፌሰር ሙራዱ አብዶ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባል በመሆን የፍርድ ቤቱን የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት በማሻሻል ሂደት ውስጥ ያላቸውን ጥልቅ የህግ እውቀት በማካፈል ከከፍተኛ የሙያ ስነ-ምግባር እና ቁርጠኝነት ጋር ላለፉት 2 አመታት የማይተካ ሚና ተጫውተዋል።

ፕሮፌሰሩ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦም ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የእውቅና ሰርተፍኬት ከምስጋና ጋር የተበረከተላቸው ሲሆን በምትካቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ጌታቸው አሰፋ ወልደማርያም ወደ አማካሪ ምክር ቤቱ ተተኪ አባል በመሆን ተቀላቅለዋል፡፡

የምክር ቤት አባላቱ በፍርድ ቤቱ እየተተገበሩ ያሉ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

Previous Article ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባል የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ
Next Article የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት እና ውይይት አደረጉ
Print
245