Tuesday, September 9, 2025 / Categories: News በሶማሌ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አሊ ባሩድ የተመራ ልዑክ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አደረገ ልዑክ ቡድኑ በነበረው ቆይታም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተከናወኑ ያሉ በርካታ የለውጥ ተግባራትና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት አፈጻጸሞች እንዲሁም አተገባበር ምን እንደሚመስል በቀን 04/13/2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ምልከታ እና ውይይት አካሂዷል ፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ በውይይቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር ፍርድ ቤቶች እንደ ሀገር መዳረሻቸው የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን በማሳደግ ተደራሽ፣ ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎት መስጠት ሊሆን እንደሚገባውና ይህንንም ለማሳካት በጋራ በመሆን የልምድ ልውውጦችን እና መልካም ተሞክሮዎችን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ አክለውም ቴክኖሎጂን መሰረት አድርገው የሚሰሩ በርካታ የለውጥ ስራዎችን የህግ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው መመሪያዎችን ማዘጋጀትና ህጉን መሰረት አድርጎ መፈጸም እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡ በውይይቱ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክሎጂ ፕሮጀክቶች የደረሱበት ደረጃ ፣ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሚና፣ የተከላካይ ጠበቆች እንዲሁም የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤቶች አደረጃጀትና አሰራር እንዲሁምየበጀት ዝግጅት የማጽደቅና የአጠቃቀም ልምዶች ላይ በርካታ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በመጨረሻም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚገኘውን የስማርት ኮርት ሩም፣ የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ ዳታ ሴንተርና ኖክ ሩም ጉብኝት ተካሂዷል፡፡ Previous Article በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቆይታ ያደረጉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ልምዳቸውን አካፈሉ Next Article የፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የችሎት ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሄደ Print 815