Monday, May 30, 2022 / Categories: News በአስተዳደር ዘርፍ የፍርድ ቤቱን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሰራተኞውን የመፈጸም ዓቅም ለማጎልበት የሰራ መሆኑ ተገለጸ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአስተዳደር ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያቀላጥፍ የአቅም ግንባታ ስልጠና 630 ለሚጠጉ የፍርድ ቤቱ የአስተዳደር ሰራተኞች ከግንቦት 04 ቀን 2014 እስከ ግንቦት 21 ቀን 2014 ዓ/ም ቢሾፍቱ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲቲዩት በአራት ዙር ሰጥቷል፡፡ በስልጠናዉ ሰራተኞች መልካም ስነ-ምግባርን ጠብቀው እንዲያገለግሉ የሙያ-ስነምግባር (work ethics)፤ ጊዜያቸዉን ባግባቡ በመጠቀም የአገልግሎት ቅልጥፍናን እንዲያሳድጉ የጊዜ አጠቃቀም (time management)፤ ሰራተኞች ከባለጉዳዮች ጋር ያላቸዉን መልካም ግንኙነት በማሻሻል የአገልጋይነት ስሜትን ለመፍጠር የደንበኛ አያያዝ (customer service) እና የጸረ-ሙስና ተግባራትን ለማጠናከር በህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ሙስናን መዋጋት (combating corruption in public organizations) በሚሉ ርእሰች ላይ ስልጠናው እየተሰጠ መቆየቱን ከስልጠና ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የስልጠና ሂደቱን ያስተባበሩት የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሙሉነህ አባተ እንደገለፁት ስልጠናዉ አገልግሎት አሰጣጥን ከማቀላጠፍና የተቋሙን ሰራተኞች የግል ስብእና ከመገንባት አነፃር ጉልህ ሚና እንደለዉ በመጠቆም የፍርድ ቤቱ ራዕይ የሆነውን የህዝብ አመኔታ የተቸረዉ ፍርድ ቤት ከመገንባት ባሻገር የዳኝነት ዘርፉን ገጽታ በመለወጥ ጠቀሜታው ከፍያለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሰራተኞችን ሁለንተናዊ አቅም መገንባት ፍርድ ቤቱ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ከያዛቸው ስትራቴጂያዊ ግቦች መካከል አንዱ ነው፡፡ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት Previous Article ሰበር ሰሚ ችሎቱ ሕጋዊነቱ ባልተረጋገጠ ሁኔታ በእስር ላይ የሚገኙት ኮሎኔል ገሙቹ አያና ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ Next Article የፍርድ ቤቱን የአስተዳር ሰራተኞች አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት የሚያጎለብቱ ስልጠናዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ Print 1862