Monday, November 17, 2025 / Categories: News በአገልግሎት አሰጣጥና የደንበኞች አያያዝ ላይ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ የፌደራል የህግና የፍትሕ ኢንስቲትዩት ለተከታታይ ሦስት ሳምንታት በሶስት ዙር ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች፣ከፍትሕ ሚኒስቴር እንዲሁም ከፌዴራል የሕግና የፍትሕ ኢንስቲትዩት ለተውጣጡ 170 የአስተዳደር ሰራተኞች ከጥቅምት 21 ቀን እስከ ህዳር 6ቀን 2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡ ሥልጠናው በየዙሩ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት አማካሪና አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ዜና ቦጋለ የስልጠናው አስፈላጊነት በገለጹበት ወቅት የአስተዳደር ሰራተኞች የአገልግሎት አሰጣጥና የባለጉዳይ አያያዝ ልህቀትን (Exellence) ለማምጣትና ግንዛቤን ለማስረጽ ያለመ በመሆኑ ሰልጣኙ ቅድመ ንቃት እንዲኖረውና በአመለካከት፣በስሜትና በብልሃት ዝግጁ ሆኖ እራሱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚረዳ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩልም አገልግሎት ሰጪው አካል ከደንበኞች አያያዝና ግንኙነት ጋር የሚኖረው የተግባቦት ክህሎት ከፍ እንዲልና እንዲሻሻል ያግዛል ብለዋል፡፡ በሁሉም ዙሮች የስልጠናው ማስጀመሪያና ማጠናቀቂያ ላይ የኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዘካርያስ ኤርኮላና ሌሎች የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢኒስቲትዩቱ የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ሰልጣኞች የወሰዱትን ስልጠና ወደ ተግባር የሚቀይሩበትን የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ Previous Article የተግባር ልምምድ (ስልጠና) በዲጂታል የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች እየተሰጠ ይገኛል Next Article በዲጂታል የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ በዋነኝነትም በኢንቲግሬትድ ኬዝ ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም (ICMIS) ሲስተም ላይ ከቀን 06-07/03/2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ሲሰጥ የቆየው የተግባር ልምምድ (ስልጠና) ተጠናቀቀ ። Print 680