Wednesday, December 11, 2024 / Categories: News በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ጋር ውይይት አደረጉ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ሶፊ ፍሮመስበርገር በቀን 02/04/2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡ አምባሳደሯ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እያከናወናቸው ባሉ የሪፎርም ስራዎች ዙሪያ እንዲሁም ወደፊት ከአውሮፓ ህብረት ጋር በጋራ ሊሰሩ የሚችሉባቸው የትብብር መስኮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር በመተባበር ያለማቸውን ዘመናዊ የስማርት ኮርት ሩም የችሎት አዳራሾችን፣ የዋይድ ኤሪያ ኔትወርክ መሰረተ ልማትን እንዲሁም ዳታ ሴንተሩን ጎብኝተዋል፡፡ Previous Article በተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ኮሚቴ አማካኝነት እየተዘጋጀ ባለው General Comment 27 on Access to Justice for children ላይ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተካሄደ Next Article ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከበረ Print 933