Friday, March 28, 2025 / Categories: News በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ አምባሳደር ክቡር ሚ/ር አሌክስ ላሜክ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ አምባሳደር ክቡር ሚ/ር አሌክስ ላሜክ -በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት በቀን 18/07/2017 ዓ.ም ጉብኝት አድርገዋል። አምባሳደሩ በነበራቸው ቆይታ በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን መሰረት አድርጎ ልዩ ችሎት የማቋቋም ሂደትን በተመለከተ እንዲሁም በሌሎች የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ስራዎች ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን በተለይም የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ትግበራ ላይ ፍርድ ቤቶች የተሰጣቸውን ሚና ለመተግበር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትብብር ማድረግ የሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በሽግግር ፍትህ ፖሊሲው ላይ በተመለከተው አግባብ ነፃ እና ገለልተኛ ልዩ ችሎት ለማቋቋም የህግ ማርቀቅ ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ለወደፊት ችሎቱን የማደራጀት ተግባር የፍርድ ቤቱ ኃላፊነት መሆኑን ፤ ረቂቅ አዋጁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከመላኩ በፊት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የህዝብ ውይይት (public consultation) ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ክቡር አምባሳደር አሌክስ ላሜክ በበኩላቸው የሽግግር ፍትህ አተገባበር ላይ ፍርድ ቤቱ እየወሰደ ያለውን ሚና በተመለከተ በርካታ ሀሳብ አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን ከእውነት ማፈላለግ ጋር በተገናኘ ከተጎጂዎች ጋር ውይይት ስለሚደረግብትና ተጠያቂነትም አብሮ ጎን ለጎን ስለሚታይበት መንገድ በማንሳት በዚህ ረገድ የሚደረገውን ስራ እንደሚደግፉ ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ላይ ውይይት በማድረግ የቴክኖሎጂዎቹ ትግበራ ምን እንደሚመስል ጎብኝተዋል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጅያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት Previous Article የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ የሁለት ቀናት ስልጠና ተሰጠ Next Article ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል Print 223