በዳኝነት ሥርዓቱ በሚታዩ ችግሮችና ሊወሰዱ በሚገባቸው የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሔደ
/ Categories: News

በዳኝነት ሥርዓቱ በሚታዩ ችግሮችና ሊወሰዱ በሚገባቸው የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሔደ

በዳኝነት ሥርዓቱ በሚታዩ ችግሮችና ሊወሰዱ በሚገባቸው የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሔደ

*************************************************************

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚደንት እና ም/ፕሬዚደንት በዳኝነት ሥርዓቱ ዙሪያ በሚታዩ ችግሮችና ሊወሰዱ በሚገባቸው የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ከሶስቱም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከተውጣጡ 150 ከሚሆኑ የፍ/ቤቶቹ አመራሮችና ዳኞች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡

ከፍርድ ቤቶቹ አመራሮችና ዳኞች ጋር የተካሔደውን የትውውቅ ፕሮግራም ተከትሎ የፍ/ቤቶችን አገልግሎት አሰጣጥ የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ከተሰብሳቢዎቹ ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ ላይ ከዳኝነት አገልግሎት አሠጣጥ ጋር ተያይዘዉ ያሉትን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ለመፍታት የዳኞችና አመራሮች አንድ ሆነዉ በትብብር መስራት አስፈላጊነት እንዲሁም ከሕዝብ የሚነሱ ቅሬታዎች በፍጥነት ምላሽ የሚያገኙበት ሁኔታ፣ ዳኞችን ፍላጎት ባማከለ መንገድ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች የሚሰጥበት ሁኔታ፣ የዳኞች የሥነ-ምግባር እና የዲሲፒሊን ጉዳይ እንዲሁም ለዳኝነት ሥራው አጋዥ የሆኑ የግብአት አቅርቦቶች ጉዳይ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ከዳኞች ጋር የተደረገዉ ዉይይት በቀጣይ ለሚሰሩት ሥራዎች እንደ ግብዓት የሚያገለግሉ ሲሆን በቀጣይም ከአስተዳደር ሰራተኞችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተመሳሳይ የውይይት መድረኮች እንደሚኖሩም ለመረዳት ተችሏል፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Previous Article በዳኝነት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከተለመደው አሠራር ወጣ ያሉ አዳዲስ አሠራሮችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ
Next Article የፌደራል ፍርድ ቤቶች በስድስት ወራት ለ84,359 መዛግብት ዕልባት መስጠታቸው ተገለጸ
Print
266