Friday, September 5, 2025 / Categories: News በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ ልዑክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጉብኝት አደረገ ልዑክ ቡድኑ ሆሳዕና ከተማ ሲገቡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በጽ/ቤታቸው የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ኤርሲኖ አቡሬ ጋር ባደረጉት ውይይት ፍርድ ቤቶች የመጨረሻ የመብት ማስከበሪያ እና የፍትሕ ምልክቶች በመሆናቸው ነፃነታቸው እና ገለልተኝነታቸው የበለጠ ሊጠናከር እንደሚገባና እንደ ሀገር ተናባቢ እና ጠንካራ የፍትህ ተቋም መገንባት እንደሚገባ እንዲሁም የዳኝነት አገልግሎቱን ዲጂታላይዝድ በማድረግ የህብረተሰቡን ፍላጎት ማሟላት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል። በቆይታቸውም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትን እና የሃላባ ከፍተኛ ፍርድ ቤትን በቀን 27/12/2017 ዓ.ም እና 28/12/2017 ዓ.ም የጎበኙ ሲሆን ከፍርድ ቤቶቹ አመራሮች እንዲሁም ዳኞች ጋር በመወያየት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። Previous Article የፍርድ ቤቶች ዲጅታላይዜሽን እና አዲሱን መመሪያ ከመተግበር አንጻር ያለዉ እንቅስቃሴን የተመለከተ ጉብኝት ተካሄደ Next Article የቪድዮ ኮንፍረንስ፣ ኢ- ፋይሊንግ እና ዳታቤዝ አገልግሎት በደቡብ ምዕራብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ቦንጋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይፋ ተጀመረ Print 312