በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት ክቡር  አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ ልዑክ የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ፣የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤትን፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳ  ምድብ ችሎት ጎበኙ።
/ Categories: News

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ ልዑክ የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ፣የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤትን፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳ ምድብ ችሎት ጎበኙ።

በጉብኝታቸውም የ2017 ዓ.ም በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በክልሉ ፍርድ ቤቶች የተጀመሩ የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ደምሴ ዱላቻ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

ገለፃውን ተከትሎም ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ዳኞችን ጋር በ2017 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም ላይ የተወያዩ ሲሆን በክልሉ ፍርድ ቤቶች የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም የዳኝነት ስርዓቱን ለማጠናከርና የህዝብ አመኔታን ለማትረፍ ወጪ ቆጣቢ እና የተገልጋዮችን እንግልት የሚቀንሱ አሰራሮች መዘርጋት ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በጉብኝቱ ባስተላለፉት መልዕክትም በክልሎች የተዘዋዋሪ ችሎቶችን የመክፈትና የማጠናከር እንዲሁም በቴክኖሎጂ የመደገፈ ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማድረግ የዜጎችን ጥያቄ መመለስ እንደሚገባ እና በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደረጃ የተሰራው የስማርት ኮርት ሲስተም እንዲሁም በውስጥ አቅም የለሙ ሲስተሞች በክልሎች ለማስፋፋት በትኩረት እንደሚሰራ ጨምረው ገልፀዋል።

የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡርአቶ ደምሴ ዱላቻ በበኩላቸው የክልሎች በቴክኖሎጂ መደገፍ በዳኝነት ሥርዓቱ ላይ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ከማስፈን ባሻገር ለዜጎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት ተደራሽነት ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወት መሆኑን በመግለጽ ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባሻገር የቴክኖሎጂዎች መሰረተ ልማቶችን ወደ ክልል ፍርድ ቤቶች በማውረድ የፍትሕ ዘርፉን ለማዘመን እየተተገበረ ያለው ስራ ውጤታማ መሆኑን አንስተዋል፡፡

Previous Article ዓመታዊ የስራ ዕቅድና አፈጻጸም እንዲሁም የሰራተኞች ፕሮግራም ተካሄደ
Next Article የፍርድ ቤቶች ዲጅታላይዜሽን እና አዲሱን መመሪያ ከመተግበር አንጻር ያለዉ እንቅስቃሴን የተመለከተ ጉብኝት ተካሄደ
Print
471