በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በቻይና የዳኝነት ልዑክ ቡድን መካከል የልምምድ ልውውጥ ተደረገ
/ Categories: News

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በቻይና የዳኝነት ልዑክ ቡድን መካከል የልምምድ ልውውጥ ተደረገ

ቻይና የዳኝነት ልኡካን ቡድን እና በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መካከል በቀን 23/12/2016 ዓ.ም የልምምድ ልውውጥ ተደረገ፡፡

በመርሃግብሩ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት፤ ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት፣ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ሚ/ር ሼን ኪንሚን፤ የሻይንጋይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ሚ/ር ጉዎ ዎይኪንግ የተገኙ ሲሆን በቻይና የዳኝነት አካል ውስጥ በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች ላይ የሚገኙ ልኡካንም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በመድረኩ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ገለጻ የተደረገ ሲሆን በተለይም የፍርድ ቤትን አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘ ከማድግ አኳያ በተሰሩ ስራዎች እና በፍትሐብሔራዊ ፍትህ አስተዳዳር ዘርፍ ትኩረት በሚሹ የለውጥ ስራዎች ዙሪያ ሠፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

የቻይና ልዑካን ቡድንም ከተደረገላቸው ገለፃ በመነሳት የአገራቸውን ተሞክሮ በስፋት ያካፈሉ ሲሆን የሁለቱን አገራት የትብብር ማዕቀፍ መነሻ በማድረግ በዳኝቱ ዘርፍም በተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ላይ በትብብር ለመስራት ይህ የልምድ ልውውጥ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም ልዑካን ቡድኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የዋይድ ኤርያ ኔት ወርክ ዳታ ሴንተርና የስማርት ኮርት ሩም የቴክኖሎጂ ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

Previous Article የወንጀል ፍትህ ስርአት ለማሻሻል በሚያስችሉ የትብብር መስኮች ላይ ከስዊድን ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ጋር ውይይት ተደረገ
Next Article የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶች ልዑክ ቡድን በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ፡፡
Print
1661