በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የለማ የኢፋይሊንግ፣ ኢሊቲጌሽንና ሰነድ ልውውጥ መተግበሪያ ላይ የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተካሄደ
/ Categories: News

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የለማ የኢፋይሊንግ፣ ኢሊቲጌሽንና ሰነድ ልውውጥ መተግበሪያ ላይ የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተካሄደ

በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የለማ በፍርድ ቤቶችና በማረሚያ ቤት መካከል ታራሚዎችን ለመፍታት የሚያስችል የመፈቻ ትዕዛዝ የሚላክበት የቴክኖሎጂ መተግበሪያ የሆነው የኢፋይሊንግ፣ ኢሊቲጌሽንና ሰነድ ልውውጥ ሲስተም ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የፌደራል ማረሚያ ቤት አመራሮች እንዲሁም የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በቀን 15/09/2017 ዓ.ም የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተካሄደ። 

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በማረሚያ ቤቶችና በፍርድ ቤቶች መካከል የነበረው የሰነድ ልውውጥ በቴክኖሎጂ ያልታገዘ በመሆኑ የግዜ እና የሀብት ብክነት ብሎም የሰነድ ዘግይቶ መድረስ የሚያመጣቸው የመብት ጥሰቶችን ለመቅረፍ ይህ መተግበሪያ ሁነኛ መፍትሄ ይዞ የሚመጣ መሆኑን ጠቅሰው ይህን መተግበሪያ በግብዓት በማዳበር ወደ ስራ በተቻለ ፍጥነት ማስገባት ለሁለቱ ተቋማት ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል የኑስ ሙሉ በበኩላቸው ይህ መተግበሪያ ለታራሚዎችም ሆነ ለተቋሙ ትልቅ ችግርን የሚቀርፍና በሰነድ ልውውጥ ወቅት የሚያጋጥሙ እንግልቶችን የሚያስቀር በመሆኑ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በማረሚያ ቤት ያለውን ችግር ለመፍታት እያደረገ ላለው ቀና ትብብርና ፈጣን ምላሽ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

መተግበሪያው የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን ለማስፍን ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው፣ ከመፈቻ ጋር በተያያዘ ያሉ የሰነድ ልውውጦችን ቀልጣፋ የሚያደርግ በመሆኑ የአግልግሎት አሰጣጡን በሁለት ተቋማት መካከል መናበብ ኖሮ እንዲሰራ ለማድረግ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ደረጃ መስራቱ የሚያስመሰግን ነው ተብሏል፡፡

መተግበሪያው እንደመነሻ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል (ገላን) መካከል የሚጀመር ሲሆን በቀጣይም በሌሎች ማረሚያ ቤቶች የሚስፋፋ ይሆናል ሲሆን እንደ መነሻ የተሰጡ ግብዓቶች ተወስደው ከተጠናቀቀ በኋላ በቅርቡ ተግባራዊ የሚሆን ይሆናል፡፡

Previous Article የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ክልላዊ ዳይሬክተር (The office of the United Nations High Commissioner for Human Rights (OHCHR) regional director) ሚስተር ማርሴል አክፖቮ የተመራ ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት
Next Article የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኞች የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ
Print
840