Monday, November 18, 2024 / Categories: News በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ረዳት ዳኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ከፌደራል ፍትህና ህግ ኢኒስቲትዩት እንዲሁም ከኢትዮጵያ አስማሚነትና ግልግል ዳኝነት ማዕከል(EMAC) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ ያተኮረ ከቀን 05/03/2017-07/03/2017 ዓ.ም ለሶስት ቀናት የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡ ለሶስት ቀናት በቆየው ስልጠና በፍርድ ቤት መር አስማሚነት የአስማሚዎች ሚና እና ክህሎት ምን እንደሆነ፣ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሂደቶች እንዲሁም የቤተሰብ አስማሚነት ላይ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የተግባር ልምምድ እንዲሁም በስኬት በአስማሚነት የተጠናቀቁ ጉዳዮች ተሞክሮ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ዳኛ አበበ ሰለሞን በመዝጊያ ንግግራቸው በአማራጭ የሙግት መፍቻ ስርዓት መዳኘት የነፃ ፍላጎት ሃሳብን መሰረት በማድረግ ሰው በህሊናው መዳኘት እንዲችል፣ የይቅርባይነት ስሜትን ለማዳበር፣ በራሱ እንዲዳኝ የማድረግ ጥበብን ለመጨመር፣ ጤናማ ግንኙነቶች እንዲቀጥል ለማድረግ እንዲሁም የፍትህ መጓደልን፣ ጊዜና ወጪን የሚቆጥብ በመሆኑ ሕብረተሰቡም ይህንን በአግባቡ እንዲገነዘብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራት እንደሚኖርባቸውና በፌደራል ፍርድ ቤቶች የአስማሚነት ስራዎችን በሚመለከት እስካሁን የተመዘገቡትን መልካም ውጤቶች በማስቀጠል ከመመሪያው አፈፃፀም አንፃር የታዩ ክፍተቶች በጥናት ማሻሻያ እንደሚደረግባቸው ገልፀዋል፡፡ አክለውም ስልጠናው የፌደራል ፍርድ ቤቶች ረዳት ዳኞች በፍርድ ቤት ያለባቸውን ኃላፊነት የሚያስገነዝብ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ሁሉም ጥረት በማድረግ አላማውን ማሳካት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡ Previous Article የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን መሰረት አድርጎ በሚቋቋም ልዩ ችሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሲካሄድ የቆየው የምክክር መድረክ ተጠናቋል Next Article የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተገልጋዮች ለፍ/ቤት የሚቀርቡ መዛግብትን ባሉበት አካባቢ ሆነው ማስከፈት የሚችሉበት (e-filing) ሶፍትዌር እና የዳኞች መዝገብ መከታተያ ( judge’s Dashboard) ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ Print 447