አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ ጸሐፊ II የመግቢያ ስልጠና ተሰጠ
/ Categories: News

አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ ጸሐፊ II የመግቢያ ስልጠና ተሰጠ

አዲስ ለተቀጠሩ ህግ ጉዳይ ጸሐፊ I እና የህግ ጉዳይ ጸሐፊ II በ ቀን 06 እና 09/06/2018 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታን እና ከለዉጥ ስራዎች ጋር ለማስተዋወቅ የመግቢያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናዉ የፍርድ ቤቶች ታሪካዊ አመጣጥ በሀገራችን፣ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ተልእኮ እና እየተካሄዱ ያሉትን የለዉጥ ስራዎች፣ የፍርድ ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ የዉስጥ አስተዳደርን የሚመለከቱ ህጎች እንዲሁም ከመብትና ግዴታዎች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ለአዲስ ተቀጣሪዎቹ የስራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን በተማሩበት የህግ ሙያ ሀገራቸውን ለማገልገል ፍርድ ቤቶችን መቀላቀላቸው ጥሩ እድል መሆኑን በመግለጽ በቅንነትና በታማኝነት በመልካም ስነምግባር ታንጸዉ ህዝባቸውን ማገልገል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

አክለውም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ትላልቅ የለውጥ ስራዎች እያከናወኑ እንደሚገኙና በተለይም በቴክኖሎጂ የተደገፉ አገልግሎቶች የሚሰጡበት ስርዓት ትግበራ ላይ በመሆናቸዉ አዲስ ተቀጣሪዎች በዚህ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መቀላቀላቸዉ እንደ መልካም አጋጣሚ በመቁጠር የለውጥ አካል መሆናቸውን አውቀዉ በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

Previous Article ሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ላይ ስልጠና ተሰጠ
Next Article በአለምአቀፍ ወንጀሎች ዙሪያ ለፌዴራል ጠቅላይ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና የማጠነቀቂያ መርሐግብር ተካሔደ
Print
338