Friday, April 7, 2023 / Categories: News አጣሪ ጉባዔው በአራት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በአራት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ሶስት ጉዳዮች ላይ ለውሳኔ አሰጣጥ እንዲያመች ተጠሪዎች መልስ እንዲሰጡበት አቅጣጫ ሲያስቀምጥ በአንድ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ተጣርተው እንዲቀርቡ ትእዛዝ በማስተላለፍ በይደር አሳልፎታል፡፡ውይይት የተደረገባቸው አራት ጉዳዮች በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አቤቱታ አቅራቢነት የቀረቡና ከአዋጅ ቁጥር 47/67 የተያያዙ የቤት /የንብረት/ ሕገ መንግሥታዊ መብትን የተመለከቱ ናቸው፡፡ ጉባዔውም በጉዳዮቹ ላይ በወቅቱ ከነበሩ አዋጆችና ደንቦች እንዲሁም ፍ/ቤቶቹ ከሰጡት ውሳኔ አንፃር በስፋት ከተወያየ በኋላ ለውሳኔ አሰጣጥ እንዲያመች በሶስቱ ጉዳዮች ላይ ተጠሪዎች መልስ እንዲሰጡበት አቅጣጫ ሲያስቀምጥ በአንዱ ጉዳይ ላይ ግን ከቤቱ ጋር ተያይዞ ጉባዔው በተለያየ መልክ ጥያቄ ያነሳባቸውንና ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ተጣርተው በቀጣይ እንዲቀርብ አሳድሮታል፡፡ጉባዔው ከዚህ በተጨማሪ በቀጣይ ስለሚካሄደው የመስማት ፕሮግራም /hearing/አጠቃላይ ዝግጅት ተወያይቶ ቀኑን በመወሰን ቀሪ ዝግጅቶች እንዲጠናቀቁ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡ Previous Article የፍርድ ቤቱ አዲስ ተሿሚ ፕሬዝዳንቶች እና በቀድሞ ፕሬዝዳንቶች መካከል የስራ ርክክብ ተፈጸመ Next Article የአውሮፓ ሕብረት ለፍርድ ቤቱ በሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ለሚከናወኑ ሥራዎች አፈጻጸም ተገቢው ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ተመለከተ Print 2093