“ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡ ህጻናት ልጆቻችን ናቸው ፍላጎታቸውን እና መብቶቻቸውን ልናከብርላቸው ይገባል”
/ Categories: News

“ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡ ህጻናት ልጆቻችን ናቸው ፍላጎታቸውን እና መብቶቻቸውን ልናከብርላቸው ይገባል”

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከUNFPA ጋር በመተባበር ከሶስቱም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለተውጣጡ ሬጅስትራሮች፣ ችሎት ፀሀፊዎች እና ችሎት ስነሰርዓት ሰራተኞች ባዘጋጀው በህጻናት ተግባቦት እና አያያዝ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ሃላፊ ዳኛ ተክለሐይማኖት ዳኜ ጽ/ቤቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ፍ/ቤቶች የህጻናትን የላቀ ጥቅም ለማስከበር ይረዳቸው ዘንድ ከሚሰሩ ስራዎች ውስጥ የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን እውቀት እና ብቃት ለማሳደግ ስልጠናዎችን መስጠት መሆኑን በመግለፅ ፣ ሰራተኞቹ ህፃናቱን እንደ ልጆቻቸው በመመልከት መብታቸውን ለማስከበር እንዲችሉ እና መልካም የሆነ የመግባባት ብቃት እንዲኖራቸው ለማስቻል ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸዋል

ስልጠናውን የሰጡት በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የማህበራዊ ሳይንስ ክፍል ለረጅም ዓመት በሀላፊነት የሰሩ እንዲሁም በህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በስነልቦና እና የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያነት በበጎ ፈቃደኝነት እያገለገሉ ያሉ ከፍተኛ የስነልቦና ባለሞያ ወ/ሮ ዘርትሁን ካሳሁን ናቸው

በስልጠናው ወቅት ለሰራተኞቹ ወደ ፍርድ ቤት በተበዳይነት፣ምስክርነት፣በወንጀል ነክ ጉዳይ ውስጥ ገብተው እንዲሁም በተለያዩ የፍትሐ ብሔር ጉዳይ የሚመጡ ህጻናት መብት እና አያያዝ ላይ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል::

Previous Article በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደር እና የዳኝነት ዘርፍ ዕቅድ አፈጻጸም እንዲሁም የአውሮፖ ህብረት ወንጀል ፍትህ አስተዳደር ማሻሻያ ፕሮጀክት አመታዊ ሪፖረት ላይ ከግንቦት 9 ቀን እስከ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት ተካሔደ
Next Article የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የእርስ በእርስ የዉይይት መድረክ በይፋ ተከፈተ
Print
389