የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህንጻ እድሳትና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ምርቃት እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት  ጉብኝት ተካሄደ
/ Categories: News

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህንጻ እድሳትና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ምርቃት እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉብኝት ተካሄደ

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የድሬዳዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የህንጻ እድሳትና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ምርቃት በቀን 11/02/2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ሱልጣን አ/ሰላም እንዲሁም የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ክቡራን ፕሬዝደንቶች ባሉበት ተካሂዷል፡፡

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ዲጂታላይዜሽን ምርቃት መድረክ በንግግር ያስጀመሩት የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ማሂር አብዱሰመድ የዳኝነት አገልግሎት ቅልጥፍናን ለማሳለጥና ተደራሽነትን ለማሳደግ በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ የተጀመሩ ዘመናዊ አሰራሮችን ሙሉ በሙሉ በመተግበር እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል የተቀመጠውን ስማርት ሲቲን የመፍጠር ግብ እንዲሳካ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በዳኝነት አገልግሎት ውስጥ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት የተገልጋይን እንግልትና የዳኞችን የስራ ጫና ከመቀነስ ባለፈ እንደ ሀገር ጠቀሜታው ዘርፈ ብዙ በመሆኑ ከፌደራል ፍርድ ቤቶች አልፎ በክልሎች በዚህ መልኩ እየተስፋፋ መሄዱ እንደ ስኬት ሊቆጠር የሚገባ በመሆኑ በሁሉም ፍርድ ቤቶች ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩልም የድሬዳዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ህንጻ እድሳት ጉብኝትና የስማርት ኮርት ሲስተም ወደ ትግበራ ምልከታ ተካሂዷል።

በዲጅታላይዜሽን ስራዉ በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እና አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢኒስቲትዩት ትብብር የለማዉና በፌዴራል ፍ/ቤቶች ስራ ላይ የዋለዉ የችሎት ድምጽን ወደ ጽሑፍ በፍጥነት የሚቀይር ስርዓት(automatic transcription) ጨምሮ የተለያዩ መተግበሪያዎችን ያካተተ ዘመናዊ ችሎት (smart court) በሁለቱም ፍ/ቤቶች ተተግብራል።

በሁለቱም መድረክ ለዲጂታላይዜሽን ስራዎቹ ስኬት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ላደረጉት አስተዋጽኦ የእውቅና ሽልማት ተበርክቷል፡፡

Previous Article በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ሲመክር የቆየው ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች መድረክ የጋራ አቋም በመያዝ ተጠናቋል፡፡
Next Article የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የሶማሊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቴክኖሎጂ ስራዎችን በይፋ አስጀመሩ
Print
623