Friday, December 5, 2025 / Categories: News የሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የልምድ ልወውጥ አደረጉ በሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰለሀዲን ቶፊቅ የተመራ የልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 25/03/2018 ዓ.ም በመገኘት የልምድ ልወውጥ አድርገዋል፡፡ በቆይታቸውም የፍርድ ቤቱን አጠቃላይ አደረጃጀት፣ የአሰራር ስርአት፣ የህግ ማዕቀፎች፣የቴክኖሎጂ ሪፎርሞች፣ ከዳኝነት ነጻነት እና ገለልተኝነት አኳያ የተሰሩ ስራዎች፣ የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም ሌሎች በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ገለጻና ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም የአቅም ግንባታን ከማሳደግ አንጻር፣ ሀገር አቀፍና የውጭ ግንኙነቶችን ከማጠናከር አኳያ የተከናወኑ ተግባራት እንዲሁም የፍርድ ቤቱ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ምን እንደሚመስሉ ልምድ ወስደዋል፡፡ በተጨማሪም ልዑኩ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለክልሉ ፍርድ ቤቶች ልምድ በማካፈልና ትብብር በማድረግ እስካሁን ላደረገው አስተዋጽኦ አመስግነው በቀጣይም ይህ ትብብር እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ Previous Article የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Ethiopia) ጋር በጋራ ስለሚሰሩባቸው ጉዳዮች ተወያዩ Next Article የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና የፌደራል የህግና ፍትህ ኢኒስቲትዩት 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስናን ቀን አከበሩ Print 416