የላይቤሪያ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትና ልዑክ ቡድናቸው በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ
/ Categories: News

የላይቤሪያ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትና ልዑክ ቡድናቸው በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ

የላይቤሪያ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ጄሚ ኩዊኪ (Honorable Jamie Quiqui Gbeisay) እና ልዑክ ቡድናቸው በቀን 17/03/2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ስራዎች ላይ ሰፊ ገለፃ የተደረገ ሲሆን የሁለቱ ሀገራት ፍርድ ቤቶች ልምዶችና የሪፎርም ስራዎች ላይም የጋራ ውይይት ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል ክቡር አቶ ጄሚ ኩዊኪ (Honorable Jamie Quiqui Gbeisay) እና ልዑክ ቡድናቸው በፍርድ ቤቱ የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራትና እየተተገበሩ ያሉ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ከጎበኙ በኋላ ፍርድ ቤቱ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም አንጻር ያለበትን ደረጃ አድንቀዋል፡፡

Previous Article በዲጂታል የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ በዋነኝነትም በኢንቲግሬትድ ኬዝ ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም (ICMIS) ሲስተም ላይ ከቀን 06-07/03/2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ሲሰጥ የቆየው የተግባር ልምምድ (ስልጠና) ተጠናቀቀ ።
Next Article ለፌደራል ፍርድ ቤቶች የቤተሰብ ችሎት ዳኞች የልምድ ልውውጥ መርሃግብር ተካሄደ
Print
406